የሃገርን ሉአላዊነት ለማስከበር ከመከላከያ ሰራዊት ለተቀላቀሉ ለ36 የዘማች ቤተሰቦች እና ለ166 የቤተሰብ አባላት የተለያዩ ድጋፍ መደረጉን በጉራጌ ዞን የእነሞርና ኤነር ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ።

የሃገርን ሉአላዊነት ለማስከበር ከመከላከያ ሰራዊት ለተቀላቀሉ ለ36 የዘማች ቤተሰቦች እና ለ166 የቤተሰብ አባላት የፍርኖ ዱቄት፣የዘይትና የማፍጠርያ የቴምር ድጋፍ መደረጉ ተጠቁመዋል።

የእነሞርና ኤነር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ያዕቆብ ግርማ በድጋፉ ወቅት እንደተናገሩት ዛሬ የተደረገው ድጋፍ የወረዳው ሕዝብና መንግስት ለዘማች ቤተሰቦች ያለውን አጋርነት ለማሳየትና በዘላቂነት ከጎናቸው እንደሆነ ለመግለጽ ነው ብለዋል።

አቶ ያቆብ አክለውም በቀጣይ ለዘማች ቤተሰቦች የሚደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍ በተቻለ መጠን ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልፀዋል።

የወረዳው ሚሊሻ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብድላ በደዊ በበኩላቸው በዛሬው እለት ድጋፍ የተደረገላቸው ለ36 የዘማች ቤተሰቦችና በቁጥር 166 ለሚሆኑ የቤተሰብ አባላት መሆኑን ጠቁመው ለእያንዳንዳቸው የተደረገው ድጋፍ እስከ 2 ሺ ብር የሚገመት እንደሆነም አመላክተዋል።

የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ሐላፊ አቶ ቸሩ ተካ በመርሃግብሩ ላይ እንደተናገሩት በዚህ ወቅት ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች በተቻለ መጠን መሰል በጎ ተግባራትን በማጠናከር መድረስ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የዘማች ቤተሰቦች በሰጡት አስተያየት ድጋፉ አስታዋሽ ወገን እንዳለቸው እንዲያስቡ እንዳደረጋቸው ጠቁመው በዚህ የፆም ወቅት የወረዳው መንግስት ላደረገላቸው ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርቧል።

በድጋፍ መርሃግብሩ ላይ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ያቆብ ግርማ ፣የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሞሸዲን አህመድ፣ የሚሊሻ ጽ/ቤት ሐላፊ አቶ አብደላ በደዊ እና የወጣቶችና ስፓርት ጽ/ቤት ሐላፊ አቶ ቸሩ ተካ መገኘታቸው መረጃው ያደረሰን የወረዳው የመንግስት ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *