የሀገር አቀፍ የ2015 የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች መረጃ በጥራት በማዘጋጀት የምዝገባ ስርዓቱን ማዘመን እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።

የሀገር አቀፍ የ2015 የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ሰርተፊኬት ፈተና የተፈታኞች ምዝገባ አስፈፃሚዎች የስልጠናና የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ ነው።

በመምሪያው የዞኑ ፈተና ዝግጅት አስተዳደር እና ትምህርት ምዘና ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አቶ መብራቴ ወልደማሪያም የምክክር መድረኩን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት የ2015 ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች መረጃ በጥራትና በወቅቱ መሙላት ይገባል።

እንደ አቶ መብራቴ ገለጻ የተማሪዎች መረጃ ሲሞላ የፊደል ግድፈት፣ የስም ስህተት፣ የጾታ ለውጥ እና የፎቶ ግራፍ ጥራት መጓደል ችግር እንዳይከሰቱ በጥራት ሞልቶ መላክ እንደሚጠበቅባቸው አቶ መብራቴ ገልጸዋል።

ደረጃውን የጠበቀ ውጤታማና ቀልጣፋ የምዝገባ ስርዓት በመዘርጋት የምዝገባ ስርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ የፈተና አስፈጻሚዎች በንቃት መሳተፍ ይጠበቅባቸዋል።

የተፈታኞች መረጃ በኦን ላየን ለመሙላት መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ መብራቴ ለአስፈታኝ ትምህርት ቤቶች በቁሳቁስ ለማሟላት ላፕቶፕ እና ዋይፋይ ማቅረቡን ገልጸዋል።

የምክክር መድረኩ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን የኢንየፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ መምህራንና ርዕሳነ መምህራን ተሳትፈዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

ዝርዝር መረጃው አ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *