የሀገር ሰላም በማስጠበቅ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ ለማስረከብ የሴቶች የላቀ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ ።

የኢትዮጵያ ሰለም አስጠብቃለሁ ለልጆቼ ምንዳ አስርክባለሁ በሚል መሪ ቀል የሴቶች የንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተካሄዷል።

በመድረኩም የተገኙ ሴቶችና ሌሎች ስራ ኃላፊዎች የደም ልገሳና በከተማ የሚገኙ የሌማት ቱሩፋቶችን ጎብኝተዋል።

በወልቂጤ ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የተዉጣጡ ከ 1 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሴቶች በመድረኩ ተሳትፈዋል።

በመድረኩ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የቤንሻጉል ጉሙዝ ክልል ዋና አፈ ጉባኤና የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ወይዘሮ አለምነሽ ይባስ እንዳሉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተመሰረተ ወራቶች የተቆጠሩ ቢሆንም የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየፈጸማቸዉ ያሉ ተግባራት የሚበረታቱ ናቸዉ።

የሀገራችን ሴቶች ለአካባቢ ሰላም መከበር ፣ለሰዉ ልጆች ነጻነትና እኩልነት መረጋገጥ፣ ለዲሞክራሲና ለመልካም አስተዳደር ሰርዓት መስፈን ድምጻቸዉን ከፍ አድርገዉ ከማሰማት ባሻገር ህይወትን አሳልፈዉ እስከመስጠት የዘለቀ ዉድ መስዋዕትነት አንደከፈሉም አብራርተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ መዋቅር ድህነትና ኋላ ቀርነትን በማሰቀረት ያደገችና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገዉ ፈርጀ ብዙ እንቅስቃሴ ዉስጥ የላቀ ሚና ከማበርከት ባሻገር የሴቶች ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አጽዕኖት ተሰጥቶት እየተሰራ እንደሆነም አመላክተዋል።

መላዉ የሊግ አባላት እንደ ሀገር ያጋጠሙ የነበሩ ፈተናዎችን በጽናት ታግሎ በመቀልበስ ፣ሰላም በማረጋገጥና በህዝቦች መካከል የነበረዉን ወንድማማችነትና እህትማማዊነት ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከርና ከፋፋይ ትርክት ለአንዴና ለመጨረሻ አሽቀንጥሮ ለመጣል በሚደረገዉ ጥረት የላቀ ሚና በመጫወት ላይ መሆናቸዉም አስረድተዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ምክተል የመንግስት ተጠሪ አቶ ይግለጡ አብዛ በበኩላቸዉ በየአካባቢዉ የሚስተዋለዉን የሰላም እጦት ለመቅረፍ የሴቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑም አመላክተዉ ይህንንም ዕዉን እንዲሆን የሴቶች ኢኮናሚያዊ ፣ፖለቲካዊና ማህበራዊ ችግሮቻቸውን መቅረፍ እንደሚገባም አስረድተዋል።

የሰላም አጦት የሚኖርበት ወቅት ዋና ተጠቂ የሚሆኑት ሴቶች እንደሆነም አንስተዉ በሁሉም አካባቢዎች ሰላም እንዲሰፍን በትኩረት ሊሰራበትም እንደሚገባም አብራርተዋል።

የጉራጌ ዞን ብልጸግ ጽ/ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ እንዳሉት ዘላቂ ሰላም በማስፈን የሴቶች ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት ማጎልበት ይገባል።

ሀገራዊ ለዉጥና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሁሉም ዜጎች ንቁ ተሳትፎና የሀላፊነት ስሜት በመላበስ ረገድ የሴቶች ሚና የጎላ እንደሆነም አመላክተዋል።

የተጀመረዉን የልማት ፣የሰላምና የዲሞክራሲ ሰርአት ግንባታ ስራዎች እዉን እንዲሆን የሴቶች ሚና ከፍተኛ እንደሆነም አመላክተዉ በዞኑና በከተማዉ ያሉ ሴቶች ከመንግስትና ከፓርቲዉ ጎን በመሆን ለለዉጡ መትጋት እንዳለባቸዉም አብራርተዋል።

የወልቂጤ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ሙባሪክ አህመድ እንዳሉት የበለጸገች ኢትዮጵያን እዉን ለማድረግ በሚደረገዉ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ዉስጥና በሰላም እሴት ግንባታ ሴቶች ግንባር ቀደም ተዋናይ እንደሆኑም አመላክተዋል።

በከተማዉ እየታየ ያለዉን አንጻራዊ ሰላም ወደ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ መላዉ ሴቶች በተደራጀና በግንባር ቀደምትነት መንቀሳቀስ እንዳለባቸዉም አስረድተዋል።

በመድረኩም የተገኙ አንዳንድ አስተያየት የሰጡ ሴቶች እንደሚሉት ለአካባቢ ሰላም ልማትና ለዉጥ እንዲመጣ የበኩላቸዉን እንደሚወጡም አስረድተዋል።

በመድረኩም የቤንሻጉል ጉሙዝ ክልል ዋና አፈ ጉባኤና የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ወይዘሮ አለምነሽ ይባስ ፣ ክብርት ወ/ሮ ኤልሳቤት ሸመልስ የማዐዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ፣ክብርት ነጅብያ ራህመቶ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ ፣ ወይዘሮ ነኢማ መኑር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ተገኝተወል።

በዞን ደረጃ የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ዋና መንግስት ተጠሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ የወልቂጤ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ሙባሪክ አህመድ
እንዲሁም የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴተች ሊግ ጸ/ቤት ሀላፊ ወይዘሪት ሲቲ አብራር ጨምሮ ሌሎችም የዞንና የከተማዉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *