የሀገራችንን ሉኣላዊነት ለማስከበር ሁሉም የክልሉ ህዝቦች አኩሪ ተግባር ፈጽመዋል- የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ እየተካሄደ በሚገኘው የክልሉ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ባቀረቡት የ6 ወራት አፈጻጸም ሪፖርት
የሀገራችንን ሉኣላዊነት ለማስከበር ሁሉም የክልሉ ህዝቦች አኩሪ ተግባር መፈጸማቸውን አስታውቀዋል ።

የክልሉ የጸጥታ ሃይል ከመከላከያ ጎን ተሰልፎ የሀገር ሉኣላዊነት ማስከበር ግዳጁን በብቃት እየተወጣ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የክልሉ ህዝብ ሀገሩን ከውጭና ከውስጥ ጠላቶች ለመጠበቅ ልጆቹን ግንባር ድረስ ከመላክ ባሻገር በአይነትና በጥሬ ገንዘብ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ያስታወቁት ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ለማስጠበቅና የግጭት አካባቢዎችን ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት መደረጉንም ተናግረዋል ።

በተለይም በእነዚህ አካባቢዎች የተካሄዱ የሰላም ውይይቶችና ኮንፈረንሶች እንዲሁም የእርቀ ሰላም መድረኮች የተሻለ ሰላም ማምጣታቸውን አቶ እርስቱ ገልጸዋል ።

በየጊዜው ለሚፈጠሩ ግጭቶች ተጠያቂ የሆኑትን ህግ የማቅረብና አጥፊዎችን ተጠያቂ የማድረግ ስራዎች ውጤት እያመጡ መሆኑን ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለሱ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉም አስታውቀዋል ።
ህገወጥ የጦር መሳሪያን ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት ከ38ሺ በላይ የጦር መሳሪያዎች ሲመዘገቡ በርካታ ህገ ወጥ መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አመላክተዋል።

በሌላ በኩልም በክልሉ በያዝነው የበጋ ወቅት 204 ሺ ሄክታር መሬት በመስኖ የለማ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 5 ሺ 1 መቶ የሚሆነው ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እንደሆነ በሪፖርታቸው አመልክተዋል ።

በክልሉ በቀጣዮቹ የበልግና መኸር ወቅት የግብርና ስራዎች የኩታ ገጠም አሰራር፣የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና የሜካናይዜችን አመራረትን ለማጎልበት በትኩረት እንደሚሰራም አስታውቀዋል ሲል የክልሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ዘግቦታል።

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *