የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከግብርና መር ወደ ኢንድስትራላይዜሽን ለማሸጋገር ተቋማት በአሰራር ሂደት ላይ ያሉ ክፍተቶች መሙላት እንዳለባቸዉ የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ እና ሳተላይት ኮሌጅ አስታወቀ።

ጥቅምት 2/2015 ዓ.ም

የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከግብርና መር ወደ ኢንድስትራላይዜሽን ለማሸጋገር ተቋማት በአሰራር ሂደት ላይ ያሉ ክፍተቶች መሙላት እንዳለባቸዉ የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ እና ሳተላይት ኮሌጅ አስታወቀ።

ተቋሙ ከባለ ድርሻ አካላት እና በስሩ ከሚገኙ ከክላስተር ተቋማት ጋር የጋራ ዕቅድ መፈራረምና ለአራት ተከታታይ ቀናት የግንዛቤ ስልጠና እንደሚሰጥም ተጠቁሟል።

የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሀይሩ አህመዲን ስልጠናዉን በንግግር ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት የሀገሪቱ ብልጽግና የሚረጋገጠዉ የጣልናቸዉ ወይም ችላ ያልናቸው በጣም ሊጠቅሙ የሚችሉ በርካታ ሀብቶች በእጃችን የነበሩና በራሳችን ጊዜ ችላ ብለን የተዉናቸዉ ነገሮች መልሰን መጠቀም ካልጀመርን ያሰብነው ልማትና ብልፅግና አይመጣም ብለዋል።

በአካባቢያችን ያሉ አባቶቻችንና ቅድመ አያቶቻችን ይጠቀሙባቸዉ የነበሩ በኛ ጊዜ ወደ ታሪክ ቅርስነት የተቀየሩና ልንጠቀምባቸዉ የምንችላቸዉ በርካታ ሀብቶች መኖራቸዉም አስታዉሰዋል።

እነዚህም እንደገና እንዲያንሰራሩ የማድረግ ስራ አንዱ የብልጽግና መንገድ እንደሆነም አብራርተዉ እንደገና እንዲያንሰራሩ ካልተደረገ ግን በተለይም በአመጋገብ ባህላችንና በአኗኗር ባህላችን ላይ ተጽኖ ይኖረዋል ብለዋል።

አሁን ባለንበት ሁኔታ በቴክኒክና ሙያ ያልተጠቀሙ የህብረተሰብ ክፍሎች መኖራቸዉም ተናግረዉ ለአብነት ያህል ቀደም ሲል ስንጠቀምባቸዉ የነበሩ የሸክላ ስራዎች መልሰን ለአገልግሎት እንዲዉሉ ማድረግና የአሁኑ ትዉልድ እሴቶችን ጨምሮባቸዉ እንደገና ሊገለገልባቸዉ እንደሚገባም አስታዉቀዋል።

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከዉጪ የሚገቡትን ቴክኖሎጂዎች ለማስቀረት እየሰሩ እንደሆነም አብራርተዉ ከዉጭ የሚገቡትን ቴክኖሎጂ በመያዝና የኛንም ጨምረንበት መሄድ ይገባል ብለዋል።

የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምክትል ዲንና የቴክኖሎጂ ሽግግርና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አስተባባሪ አቶ ቦጋለ ተክሌ በበኩላቸዉ እንዳሉት አዳዲስ የአሰራር ስርአቶችን በመፍጠር በቴክኖሎጂዉ ፈጠራዉ ዘርፍ ዉጤታማ ስራዎችን መስራት ይገባል።

ኮሌጁ አገልግሎት ከሚሰጧቸዉ ተቋማትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የአገልግሎት አሰጣጣችን ምን እንደሚመመስል የጋራ ዉይይቶችና አካሄዶች ላይ መነጋገርና ተቋማት ተግባሮቻቸዉን ለመፈጸም የሚጠቀሙባቸዉን አሰራሮች ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተሰራ እንደሆነም አስታዉቀዋል።

በዚህ መሰረት ከግብርና ፣ ከኢንተርፕራይዞች ልማት ጽህፈት ቤት ፣ከዩኒቨርሲቲ ፣ከምርምር ተቋማት፣ ከምርጥ ዘር ምርምር እንዲሁም በፖሊ ቴክኒክ ስር ያሉ ሌሎች የክላስተር ተቋማት ዲኖች እና አሰልጣኞች የተገኙበት ስልጠና እንደሆነም አብራርተዋል።

የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከግብርና መር ወደ ኢንድስትራላይዜሽን ለማሸጋገር ተቋማት እየሰሩ እንደሆነም የገለጸት አቶ ቦጋለ በአሰራር ሂደት ላይ ያሉ ክፍተቶች ከግብርና ባለሙያተኞች ጋር በመሆን የመለየት ስራ ወይም የግብርናዉ ስራ እንዴት ማዘመን እንዳለብን የእሴት ሰንሰለትን ስራ ይሰራል ብለዋል።

ይህም የማህበረሰቡ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ለመፍጠር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል የኢንተርፕራይዝ ጽህፈት ቤት ባለሙያተኞችም አመራሮች ወደ ማህበረሰቡ የሚደርሱ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች በኢንተርፕራይዞች በኩል ምን እየተሰራ እንደሆነ አይተዉ በማገዝ የተሻለ ነገር ለመፍጠር ባለድርሻዎች በስልጠናዉ መሳተፋቸዉ ያግዛል ብለዋል።

ተቋማት የሚሰሩት የአሰራር ክፍተት ጠንካራ ጎኖች ከነዚህ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለይተዉ ቀጣይ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ስልጠናዉ አጋዥ እንደሆነም ጠቁመዋል።

ኮሌጁ ከባለ ድርሻ አካላት እና በስሩ ከሚገኙ ከክላስተር ተቋማት ጋር የጋራ ዕቅድ መፈራረምና የግንዛቤ ስልጠና ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል ይሆናል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነዉ።

ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *