የሀገሩን ህልውና ለማስከበር ቤተሰቡን ጥሎ ሀገሩን አስቀድሞ ለኢትዮጲያ ሉአላዊነት እራሱን ሊሰውት ለሄደ ወታደር ቤተሰቡን ከዝናብ፣ከውርጭ፣ከፀሀይ ጨረር፣ከብርድ እና ከቆፈን መታደግ የኛ ሃላፊነት ነው ሲሉ በጉራጌ ዞን የማረቆ ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ ኑጉሴ መኬ ገለፁ።

ነሀሴ 15/2014 ዓ.ም

የሀገሩን ህልውና ለማስከበር ቤተሰቡን ጥሎ ሀገሩን አስቀድሞ ለኢትዮጲያ ሉአላዊነት እራሱን ሊሰውት ለሄደ ወታደር ቤተሰቡን ከዝናብ፣ከውርጭ፣ከፀሀይ ጨረር፣ከብርድ እና ከቆፈን መታደግ የኛ ሃላፊነት ነው ሲሉ በጉራጌ ዞን የማረቆ ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ ኑጉሴ መኬ ገለፁ።

በጉራጌ ዞን በማረቆ ወረዳ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በተለያዩ የበጎነት እሴቶች ላይ መሠረት በማድረግ በከተማ እና በገጠር ቀበሌያት ከ12ሺ በለይ የበጎ ፍቃድ ወጣቶችን በማስተባበር ከመንግስትና ከህብረተሰብ የሚወጣ 9 ሚለየን ያህል ገንዘብ ለማስቀረት በተደራጀ የሰው ሃይል እየተሰራ መሆኑን የበጎ ፍቃድ ቴክኒክ ኮሚቴ አስታውቋል።

በትናትናው ዕለትም የዘማች የአቶ ደሴ ስራቶ ቤተሰብ እና ለወ/ሮ ጀሚላ ከማል 33 ቆርቆሮ አዲስ ቤት እየተሰራላቸው እንደሚገኝ እና ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚደረግ የማረቆ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ም/ሃላፊ እና ወጣት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ሁሴን ሂሳቦ አስታውቀዋል።

የዘማች ደሴ ስራቶ ቤተሰቦች በበኩላቸው ከዚህ በፊት የነበረው ቤት ከማርጀቱ የተነሳ ለዝናብ ለብርድ የተጋለጠ እንደነበረ እና መቼ ለመቼ በላያችን ላይ ይወድቃል በሚል ስጋት ውስጥ ይኖሩ እንደነበር ገልፀው አሁን በተደረገው ድጋፍ ደስተኛ መሆናቸውን ያብራሩ ሲሆን የወረዳውን የበጎ ፍቃድ ቴክኒክ ኮሚቴን እና ባጠቃላይ ለዚህ በጎ ተግባር አሻራቸውን ያኖሩቱን በሙሉ እጅግ አድርገው አመስግነዋል።

ወ/ሮ ጀሚላ ከማል የ5 ልጆች እናት እና ምንም ስራ የሌላት አቅመ ዳካማ ሴት ሲሆኑ ባለቤታቸው በስራ ጉዳይ ሰው ሀገር ሄዶ በመሞቱ ምክንያት ለብዙ ስቃይና እንግልት ተዳርገዋል።

ያብቻም አይደለም የነበሩበት ትንሽዬ ጎጆ ቤት በመፍረሷ ከነ ልጆቿ ውጪ ላይ ያድሩ እንደነበረ ገልፀው ለስደት በተነሳንበት ወቅት አቶ ኤርመንቾ ካሰሞ የትም አትሄዱም ብሎ ሁኔታዎች እስኪመቻቹ ድረስ ከብርደ እና ከዝናብ ታድጎናል በማለት እንባ በተናነቀው ስሜት ስለ ነበሩበት ሁኔታ አስረድተውናል።

ወይዘሮ ከድቻ ከማል አሁን በወረዳው በጎ ፍቃድ ቴክኒክ ኮሜቴ አማካኝየት እየተሰራላቸው ያለው አዲስ ቤት ያላሰቡትና ያልገመቱት በመሆኑ ደስታቸው ወደር እንደሌለው በመግለፅ ይህን ላደረጉ ቅን እና ደጋግ ሰዎች ጠዋት ማታ ማመስገን መመረቅ ስራዬ ሆኗል በማለት ደስታ በተሞላበት ስሜት ስለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን ገልፀዋል።

የማረቆ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኑጉሴ መኬ በበኩላቸው የሀገሩን ህልውና ለማስከበር ቤተሰቡን ጥሎ ሀገሩን አስቀድሞ ለኢትዮጲያ ሉአላዊነት እራሱን ሊሰውት ለሄደ ወታደር ቤተሰቡን ከዝናብ፣ከውርጭ፣ከፀሀይ ጨረር፣ከብርድ እና ከቆፈን መታደግ የኛ ሃላፊነት ነው ብለዋል።

በተያያዘ ዜናም ወ/ሮ ከድቻ ከማልም የነበሩበት ሁኔታ እጅግ የሚከብድ እና ሰዕባዊ እገዛ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ከነ ልጆቿ ሜዳ ላይ እንዳትወድቁ ለማድረግ አዲስ ቤት ሰርተን እናስረክባለን በማለት ገልፀዋል።

አቶ ኑጉሴ አክለውም በጎነት የቆሰለ ህሊናን ያክማል የአቅመ ደካሞችን ህይወት ያለመልማል በመሆኑም ዙሪያችንን እንቃኝ የኛ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው እጅግ በከባድ ህይወት ውስጥ የሚኖሩ በርካታ ሰዎች በየ አከባቢያችን ያሉ በመሆኑ አቅማችን የቻለውን የሰዕባዊነት እጅቻችንን እንዘርጋ መልካምን መልሶ ይከፍለናል በማለት አብራርተዋል።

በዘንድሮ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት መረሃ ግብር እስካሁን ድረስ ከመንግስት የሚወጣ 1.5 ሚለየን ብር ማዳን መቻሉን እና ከ12ሺ በላይ ወጣቶች የተሳተፉበት መሆኑ የማረቆ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ም/ሃላፊ እና ወጣት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ሁሴን ሂሳቦ ተናግረዋል።

በከተማ እና በገጠር ቀበሌያት ላይ የአረጋዊያን ማሳ መንከባከብ፣የደም ልገሳ፣የአረንጓዴ አሻራ ተግባር፣የቤት ማደስ እና አዲስ ቤት የመስራት መሰል በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎች በወረዳው እየተሰሩ እንደሆነ ም/ሃላፊ እና ወጣት ዘርፍ አስተባባሪው አቶ ሁሴን አብራርተዋል ሲል የዘገበው የማረቆ ወረዳ የመንግስት /ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ነው።

መረጃዎቻችበተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *