የሀዋሪያት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ለማሟለት እንዲቻል ለሚያግዙ አካላት ሁሉ ጥሪ ቀርቧል።

የሀዋሪያት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አቅም ለማሳደግ #አዲስዓመት ለአዲስስኬት በሚል አጀንዳ #ለሆስፒታላችንእናዋጣለን❗️ በሚል መሪ ሀሳብ ከሀዋሪያት ከተማ ነዋሪዎች ጋር ማለትም ከንግዱ ማህበረሰብና ከመንግስት ሰራተኞች ጋር የምክክር መድረክ ተካሄዷል።

በምክክር መድረኩ የተገኙት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብስራት ገብሩ እንደተናገሩት የወረዳው ማህበረሰብ በወረዳው ታቅደው የሚሰሩ የልማት ስራዎች ለማሳካትና ወደ ውጤት ለማሻገር ያልተቆጠበና ሁሉ–ዓቀፍ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ በማቅረብ ለእስካሁኑ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

የሀዋሪያት የመጀመሪ ደረጃ ሆስፒታል በ18 ህንፃዎች በ195 ክፍሎች የተዋቀረ እንደሆነና ከ53 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በኩል የክልልና የዞን መንግስት ሚናቸውን መወጣታቸው ተናግረዋል።

አያይዘውም የሆስፒታሉ የቁሳቁስ ችግር ለመቅረፍ ከወረዳው የማህበረሰብ፣ ወልቂጤ ዩንቨርስቲ እና ኢትዮ – ኢንጅነሪንግ ግሩፕ ከመንግስት ጎን በመሆን ያደረጉት አበርክቶት ከፍተኛ እንደነበር በማቅረብ በታዳሚው ዘንድ ምስጋና ቀርቧል።

የሆስፒታል አንኳር ችግሮች የህክምና መሳሪያዎች እጥረት፣ እንጨትና የእንጨት ውጤቶች አለመሟላት እና የተለያዩ ዓይነት የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች ጉድለት መሆኑን በዝርዝር ቀርቦ የቅድምያ ቅድምያ ለህክምና መሳሪያዎች ግዢ መስጠት እንደሚያስፈልግ ጠቁመው ከ45,308,800 ብር በላይ ወጪ ለማሰባሰብ በዕቅድ መቅረቡን አብራርተዋል።

ለሆስፒታሉ የቁሳቁስ እጥረት ለማሟላት የከተማው ነጋዴዎች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ የወረዳው ተወላጅ የሆኑና በአገር ወስጥም ይሁን በውጭ አገር የሚገኙ ሁሉ ዓረዓያ ሆነው እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

በዚህ ድጋፍ በጉራጌ ዞን የሚገኙ መዋቅሮች፣ የመንግስትና የግብረ -ሰናይ ድርጅቶችም እንደሚተባበሩ በመተማመን የምሁር አክሊል ወረዳ ህዝብና መንግስት ትልቅ ተቋም የሆነውን የሀዋርያት የመጀመሪያ ሆስፒታል ያለምንም ስስት በመለገስ ለህዝባችን ያላቸው ድጋፍና አጋርነት አጠናክረው እንዲቀጥሉ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብስራት ገብሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ሆስፒታሉ ለመደገፍ በምክክር መድረኩ ላይ የተሳተፉ ነዋሪዎች እጅግ ግሩምና ድንቅ ሀሳባቸው በማቅረብ ቃል መግባት ችለዋል።

በተከታታይ ጊዜም ለመደገፍም ሆነ ሌሎችን ለማስተባበር ያሳዩት ዝግጁነትና ዓረዓያነት ይበል የሚያሰኝ በሆኑም መድረኩ ሲጠቃለል በኮሚቴዎች በኩል ላቅ ያለ ምስጋ ቀርቧል።

ሆስፒታሉ በሙሉ አቅሙ ወደ አገልግሎት ለማምጣት የተጓደሉና ጊዜ የማይሰጡ የህክምና መሳሪያዎች ለማሟላት በበጎነት የሚሳተፉ አካላት ከጎናችን እንዲሰለፉ በሚል በተሳታፊዎች በቅንነት ሀሳቦች ተነስተዋል።

ለማህበረሰቡ ዘላቂ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ኖሮን ሲያበቃ የህክምና መሳሪያዎች ባለመሟላታቸው እያጋጠመን ያለው እንግልት ለማቃለል እኛ የምናደርገው አስተዋፅዖ እንዳለ ሆኖ ሌሎች ወገኖቻችንም፣ መንግስታችን ሊደግፈን ይገባል ሲሉ በምክክር መድረኩ የተገኙት ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

ሆስፒታሉ ለመደገፍ እንዲቻል በሀዋርያት የመጀመሪያ ሆስፒታል ስም የተከፈቱ አካውንቶች ከታች የተቀመጡት ናቸው።
👉 CBE 1000650277523
👉NIB 7000054845068
✔ ሁሉም በሚችለው እንዲደግፍ፤ ለወገን የሚጠበቅበትን አስተዋፅዖ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

ዘገባው የወረዳው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *