ዜጎች የሚጠይቁትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በአጭር ጊዜ ምላሽ ለመስጠት ወቅቱን የሚመጥን የአገልግሎት ስርአት በመዘርጋት መስራት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ፐብሊክ ሰርሺስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያው በዞኑ ለሚገኙ ለቀበሌ ስራ አስኪያጆች የሪፎርምና የመልካም አስተዳደር ባለሙያዎች በሴክተር ተኮር ሪፎርም አተገባበር፣ በመሰረታዊ ስራ አመራር፣ በስነ-ምግባርና በመልካም አስተዳደር እቅድ አስተቃቀድ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በወልቂጤ ከተማ ተሰጥቷል።

የጉራጌ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ዙልፋ አለዊ በስልጠናው መድረኩ ተገኝተው እንደገለፁት መንግስት የቀረፃቸው የተለያዩ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን ተፈፃሚ እንዲሆኑ የቀበሌ ስራ አስኪያጆች በስራቸው የሚገኙትን መዋቅሮችን በተገቢው በመምራት የህብረተሰቡን የአገልግሎት አሰጣጡ የተሻለና ቀልጣፋ በማድረግ መስራት እንዲችሉ ስልጠናው ወሳኝ ነው።

ከዚህ በፊት መንግስት የዘረጋቸው አሰራሮች ለውጡን መነሻ በማድረግ የተለያዩ ትችቶችንና ቅሬታዎች ከማቅረብ በተጨማሪ ተቋማት የአሰራር ስርአቱ በመከተሉ ረገድ ውስነት ስለነበረባቸው አሁን ላይ የተሻለ የሪፎርም ስራ በመስራት ተቋማት እንደየተቋሞቻቸው ተግባር መነሻ በማድረግ ቲም ሞዴል በመቅረፅና በማጠናከር እንዲሰሩ ተደርጓል ብለዋል።

የቲም አሰራሩም ውጤታማ በሆነ መንገድ ወደ ቀበሌ ድረስ በማውረድ ስራ አስኪያጆች በበላይነት በመምራትና በመከታተል ተግባራዊ እንዲሆን መስራት አለባቸው ብለዋል።

ስልጠናውም በቀበሌ ደረጃ የተሻለ እቅድ እንዲያቅዱ፣ ከህብረተሰቡ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር እቅዶችን ለይተው እንዲያቅዱ፣ የቀበሌ ስራ አስኪያጆችን ሀላፊነትና ተግባር ጠንቅቀው በማወቅ እንዲፈፅሙና ከዜጎች የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አፈታት ላይ በቂ ግንዛቤ በመጨበጥ በቀጣይ ህብረተሰቡ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል እንደሆነም ገልፀዋል።

ዜጎች የሚጠይቁትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በአጭር ጊዜ ምላሽ ለመስጠትና ህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኝ ወቅቱን የሚመጥን የአገልግሎት ስርአት በየተቋሞቻቸው በመዘርጋት መስራት አለባቸው ብለዋል።

በተለይም ከየታችኛው መዋቅር ያላቸው የመንግስት ተቋማት ግብርና፣ ትምህርትና ጤና የመሳሰሉ ተቋማት ከመምሪያው ውል የገቡበት ሞዴል ለታችኛው መዋቅር በማውረድ ከስራ አስኪያጆች ጋር በመቀናጀት በባለቤትነት ሊፈፅሙት እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ቀበሌዎች በተሻለ ደረጃ ከፍ እንዲሉና ህብረተሰቡ ተሳታፊ በሚሆንባቸው ጉዳዮች ላይ በንቃት በማሳተፍ የተቀናጀ ስራና ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

አቶ ተከተል ገዛኸኝ ስልጠና በሰጡበት ወቅት እንዳሉት ሰልጣኞች በስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ በቀጣይ በየተቋሞቻቸው ወስደው ተግባራዊ በማድረግ ግንባር ቀደም መሆን አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል።

በቀበሌ ደረጃ ያሉ መዋሮችን በአሰራር ስርአቱ መሰረት እቅድ አቅደው ህብረተሰቡ ማገልገል እንዳለባቸው ጠቁመው በዚህም ስራ አስኪያጆች የበላይነት በመውሰድ ህብረተሰቡን የሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በተገቢው በመያዝና በማደራጀት ምላሽ ለመስጠት መስራት አለባቸው ብለዋል።

አቶ ኑርአህመድ ሙሰማ ከጉመር ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ ፅህፈት ቤት ፣አቶ ዲልታታ አሊዬና ወይዘሪት ረድኤት ሙሉጌታ የምስራቅ እምበር ቀበሌና የሰላም ቀበሌ ስራአስኪያጆች ሲሆኑ በጋራ በሰጡት አስተያየት በስልጠናው በቂ ግንዛቤ እንዳገኙበትና ከዚህ በፊት የነበረባቸውን የክህሎት ክፍተት እንደሞላላቸውም ገልፀዋል።

በስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ በቀጣይ በየተቋሞቻቸው ወስደው ተግባራዊ በማድረግ የተሻለና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ህብረተሰቡ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚያነሳቸውን ቅሬታዎችን በቀጣይ ምላሽ ለመስጠት በቁርጥኝነት እንደሚሰሩም ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ነው።

= ኢትዮጵያን እናልማ፣የፈረሰውን እንገንባ፣ ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36C

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *