ዘመኑ ያፈራቸው የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ፓርቲው እየሠራቸው ያሉ ስራዎችን የማስተዋወቅና ሀሰተኛ መረጃዎችን የመከላከል ስራ በትኩረት እንደሚሰራ የጉራጌ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ገለፀ።

ፓርቲው መሠረታዊ በሆኑ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምና በህዝብ ግንኙነት ስራዎች ዙሪያ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ከወረዳና ከተማ አስተዳደር ለተውጣጡ አካላት በወልቂጤ ከተማ ሰጥቷል።

ህዝብን ከህዝብ ሊያጋጩ የሚችሉ አጀንዳዎችን በትክክለኛና እውነተኛ መሆነ መንገድ መታገል እንደሚገባ የመድረኩ ተሳታፊዎች ገለፁ።

የጉራጌ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ምክትል የመንግስት ተጠሪ ኃላፊ አቶ ክብሩ ፈቀደ በመድረኩ እንደገፁት በፓርቲው ፕሮግራምና መሠረት በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ ዘሮፎች ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ዘመኑ ባፈራቸው የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ከማስተዋወቅ ረገድ በየደረጃው ያሉ የፓርቲው አመራሮችና ኃላፊውች በነቃት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

በማህበራዊ ሚዲ ባልተገባ መልኩ የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎችን በፓርቲው ሀገራችንን ሊያሻግሩ በሚችሉ በፓርቲው በእወነተኛ እሳቤዎች ታግለን ማሸነፍ ይገባል ብለዋል።

የወጣቶችና የሴቶች ሊግ አደረጃጀት ለወጣቱ የጠራና ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ትክከለኛ መረጃ በማስገንዘብ ረገድ የማይተካ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

በአመራሩ በየደረጃው የመሪነት ሚናውን በአግባቡ እንዲወጣና የተጠያቂነት አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ በተጨባጭ ተግባራዊ ማድረግ ፓርቲው አየሰራ ነው ብለዋል።

በጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብረሀም ጠና ስልጠናውን ሲሰጡ እንዳሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ዘርፍ የሚሰሩ የህዝብ ግንኙነት ስራዎች ዙሪያ የወረዳውና ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የፖለቲካ ሪዕዮት አለም ኃላፊዎች እና የወጣቶችና የሴቶች ሊግ ኃላፊዎች ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ግንዛቤ ለማስጨበጥና በትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ የገጽታው ግንባታው ላይ የበኩላቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ያሰበ ስልጠና ነው ብለዋል ።

የብልፅግና ፓርቲ እንደ ሀገር ህዝቡን ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ ገዙፍ ፕሮጀክቶችን አቅዶ እየሠራ ያለ ፓርቲ ነው ያሉት አቶ አብረሀም ሆኖም ባልተገባ መልኩ በማህበራዊ ሚዲያ የሀሰት መረጃዎች አየተሰራጩ ህብረተሰቡን የማሳሳት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በመሆኑም እነዚህ የሀሰት መረጃዎች ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ፣ ህዝብ ከመንግስት የሚነጥሉና ሰላምና ልማት እንዳይፋጠን የሚያደርጉ በመሆኑ የፓርቲው አመራርና አባል አውነተኛ መረጃዎችን ለህዝቡ በማድረስ መከላከል ይገባል ብለዋል።

የብልፅግና ፓርቲ በዞኑ አንድ ሺ አርባ አራት መሠረታዊ ድርጅት 9ሺ 7 መቶ ህዋሳት ያሉት በእነዚህ ስር 285ሺ 607 አባላት እንዳሉት የገለፁት አቶ አብረሃም የንቅናቄው መድረክ በወረዳና በከተማ አስተዳደር ደረጃ አስከታች አባል ድረስ የሚቀጥል ነው ብለዋል።

ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል አቶ መሀመድ ፣አቶ አበበ አገዘ እና ወ/ሮ ሙንተሀ ሽሁር በጋራ በሰጡት አሰተያየት መደረኩ ወቅቱን የጠበቀና በአሁኑ ሰዓት ሀይማኖት ከሀይማኖት ብሄር ከብሔር ለመጋጨትና ሀገርራችን ችግር ውስጥ እንድትገባ ማንነታቸውን ደብቀው የሚንቀሳቀሱ በርካታ በመሆናቸው መላው ህብረተሰብ ሊታገላቸው እንደሚገባ ገልጸዋል።

እንደፓርቲ ትክክለኛና ታዓማኔነት ያለው መረጃ በተከፈቱ ገጾች በመልቀቅ መላው አባሎችና አመራሮች በነቃት በማሳተፍ ትክክለኛ መረጃ ለህዝቡ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት ሊሰራ ይገባ ብለዋል።

በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ ዘዴዎች በማበልጸግና በመጠቀም የፓርቲው እሳቤዎችን ለማስረፅ እና የተሰሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን አጉልቶ ለማውጣት የነቃ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ መግለጻቸውን የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *