ዋን ዋሽ የበጀት ድጋፍ በጤና፣ በትምህርትና በውሃ ላይ የሚስተዋሉትን ችግሮች በተወሰነ ደረጃ በመቅረፍ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ፡፡

ሰኔ 22/2015 ዓ.ም

ዋን ዋሽ የበጀት ድጋፍ በጤና፣ በትምህርትና በውሃ ላይ የሚስተዋሉትን ችግሮች በተወሰነ ደረጃ በመቅረፍ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ፡፡

በዞኑ በዋን ዋሽ የሚከናወኑ ተግባራት ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል፡፡

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በውውይቱ ላይ እንደገለጹት በዋን ዋሽ የሚከናወኑ ተግባራት ውጤታ ለማደረግ እንዲቻል በበጀት አመቱ መጀመሪያ ላይ የሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ያሳተፈ ዕቅድ ከማቀድ ጀምሮ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተቀናጅተው ሊሰሩ ይገባል ፡፡

ይህ ፕሮጀክት ቀጣይነት እንዲኖረው እና ወደ ሌሎች ወረዳዎች ለማስፋት እንዲቻል በዋን ዋሽ የታቀፉ ወረዳዎች በፕሮጀክቱ ተግባራዊ እንዲሆኑ የታቀዱ ተግባራት አፈጻጸም ውጤታማ በማድረግ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ማድረግ እንዳለባቸው ዋና አስተዳዳሪው አስገንዝበዋል፡፡

የበጀት እጥረት ምክንያት በማድረግ በግንባታዎች ላይ የሚስተዋሉትን የጥራት ጉድለቶች ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ሊቀረፉ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ጉግሳ በውይይቱ ላይ እንዳሉት ዋን ዋሽ የበጀት ድጋፍ በጤና፣ በትምህርትና በውሃ ላይ የሚሰተዋሉ ችግሮችን በተወሰነ ደረጃ በመቅረፍ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ ነው፡፡

በዋን ዋሽ ተጠቃሚ የሆኑ ወረዳዎች በፕሮጀክቱ የታቀዱ ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት ከዞን ጀምሮ በቅንጅት ያለመስራት ችግር ሊቀረፍ እንደሚገባ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በፕሮጀክቱ የታቀፉት እንደጋኝ፣ ቀቤና፣ ማረቆ፣ ሶዶ፣ ምህር አክሊል፣ ገደባኖ ጉታዘር ወለኔና ጉመር ወረዳዎች በጤና፣ በትምህርትና በውሃ የተሻለ አፈጻጸም ሊያሳዩ ይገባል ሲሉ አቶ ሰለሞን ጉግሳ ገልጸዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በመንግስት በጀት ሊቀረፉ የማይችሉ ችግሮች በተለይ በጤና፣ በትምህርትና በውሃ ላይ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ ዋን ዋሽ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

በቀጣይ በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ በሆኑ ወረዳዎች ማቺንግ ፈንድ በመባል ሚታወቀውን የበጀት ድጋፍ በወቅቱ ለማስተላለፍ እና በዋን ዋሽ የሚከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር ተቀናጅተው እንደሚሰሩ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *