ዋቻበያ ፏፏቴ

ዋቻበያ ፏፏቴ

በጉመር ወረዳ ከሚገኙ ድንቅ የተፈጥሮ መስህቦች ውስጥ አንዱ ዋቻበያ ፏፏቴ ነው።

ይህ ፏፏቴ በጌታና በጉመር ወረዳዎች ድንበር በጉመር ወረዳ አርሟ ቀበሌ ውስጥ ይገኛል።

ውንቐ ወንዝ የዚህ ፏፏቴ መገኛ ሲሆን ቦታውም በድሮ ጊዜ ባድ አምልኮ ይፈፀምበት ነበር።

ዋቻበያ በጭሽትና በንፗር የዋቅ የአምልኮ ስርአቶች በተለይ ከጌታ ወረዳ የፈኘቅር ቀበሌ ነዋሪዎች እርድ በብዛት የሚከወንበት ስፍራም እንደነበር ይታወቃል።

በጉመርና በጌታ ወረዳ አመቱን በሙሉ ከሚፈሱ ወንዞች ግንባር ቀደም ተጠቃሽ የሆነው የውንቐ ወንዝ የተለያዩ ገባር ወንዞች እየጨማመረ ቸሃን ወረዳን አቋርጦ ዋቤ ወንዝ መድረሻው ያደርጋል።

ይህ ወንዝ መነሻው ጘታ ወረዳ ቢሆንም እየሄደ እየሄደ ጉመርና ጌታ ወረዳዎች ለሁለት ከፍሎ ቸሃና እኖር ወረዳዎች አጠጥቶ ጊቤ ወንዝ ይቀላቀላል።

ከጉመር አርሟ ቀበሌ ከጌታ ፈኘቅር ቀበሌ የወንዙ ተጠቃሚ የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው።

በቀጣይም ሁለቱም ወረዳዎች ተቀናጅተው ይህን ወንዝ ለመስኖ ስራ እንዲውል በማድረግ ትልቅ አቅም ፈጥሮ ህብረተሰቡ ማስጠቀም ስለሚቻል ትኩረት ሊሰጠው ይገባል መልዕክታችን ነው።

ምንጭ -የጉመር ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/ፅ/ቤት

በረጃ ምጭነት ገፃችንን ስለምትከታተሉ እናመሰግናለን!
እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *