ወጣቶች ከተለያዩ መጤ ባህሎች ተጠብቀው ስራ ፈጣሪና ሀገር ወዳድ እንዲሆኑ በትኩረት መስራት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያው የወረዳና ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የ2014 ዓመተ ምህረት የ9 ወር ዕቅድ አፈጻጸም በወልቂጤ ከተማ ገምግሟል።

በግምገማ መድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አወል ጅማቶ ከአጠቃላይ የሀገሪቱ ህዝብ ብዛት ሰላሳ በመቶ የሚሆኑት በወጣትነት የእድሜ ክልል የሚገኙ ሲሆን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ዘዋሪ ሀይል እንደሆኑም ይታወቃል።

ወጣቱ ያለውን እውቀት፣ ጉልበትና ጊዜ በአግባቡ በመጠቀም ከራሱ አልፎ ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ የሚጠበቅበትን ሀላፊነት መወጣት ይጠበቅበታል ብለዋል።

አያይዘውም አቶ አወል ወጣቶች በተለያዩ መጤ ባህሎች ተጽዕኖ ስር እንዳይወድቁ በማድረግና የራሳቸዉ ታሪክ ወግና ባህል አክብረው በጥሩ ስነ ምግባር ታንጸዉ ስራ ፈጣሪና ሀገር ወዳድ እንዲሆኑ በትኩረት መስራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል ።

ወጣቶች ጊዜያቸው በአልባሌ ቦታ እንዳያውሉ የስፖርት ማዞዉተሪያ ስፍራዎችን በሁሉም አካባቢዎች ማዘጋጀት ይገባል ያሉት አቶ አወል በስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ግንባታ የሀብት አሰባሰብ ስራ ላይ የሚስተዋሉ ዉስንነቶች ለመቅረፍ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

በጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ድንቁ በበኩላቸዉ በዞኑ በወጣቶች የሚተገበሩ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች በማስቆምና ወጣቱን ከሱስ ነጻ በማድረግ አምራች ሀይል እንዲሆኑ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባም አብራርተዋል።

የወጣቱ ስብዕና ግንባታ ማዕከል በስፋት በመስራትና በዘርፉም የሚፈለገዉ ዉጤት እንዲመጣ ባለድርሻ አካላቶች አጽንኖት ሰጥተዉ መስራት እንዳለባቸዉም አመላክተዋል።

በጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አደም ሽኩር እንዳሉት የወጣቶች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የስፖርት ማዘዉተሪያ ስፍራዎች ማዘጋጀት እንደሚገባና በየአካባቢዉ ያሉ ወጣት መዋያ ጥርጊያ ሜዳዎች ማመቻቸት ይገባል ብለዋል።

ስፖርቱ ህዝባዊ መሰረት በማስያዝና በዘርፉ የሚፈለገዉ ዉጤት እንዲመጣ ቅንጅታዊ አሰራሩን የበለጠ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አብራርተዋል።

በዞኑ በወጣቶች የበጎ ፈቃድ በርካታ ስራ እየተሰራ መሆኑ ገልፀው አሁንም በበጋ በጎ ፍቃድ አገልግሎት ለአረጋዉያንና ለአቅመ ደካሞች አዲስ ቤት ግንባታና የጥገና ስራዎችና በሌሎችም ተግባራት ላይ ዉጤታማ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

ለወጣቶች ምቹ የመዝናኛ ማዕከል ግንባታ ላይ ያሉ ጉደለቶችን በቀጣይ በማረምና የስፖርት ማዘዉተሪያ ስፍራዎች በማመቻቸት ረገድ የሚታዩ ዉስንነቶችን መቅረፍ እንደሚገባም አስረድተዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በየደረጃው የወጣቱ ስብዕና ለመገንባትና ከመጤ ባህል ለመታደግ የወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያና መዝናኛ ስፍራዎች በማጠናከር ወጣቶች ለራሳቸውና ለሀገራቸው እድገት የበኩላቸው እንዲወጡ በቅንጅት እንደሚሰሩም ገልፀዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነዉ።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

=ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *