ወጣቱ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ለይቶ በማደራጀት ፈትሀዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ የጉራጌ ዞን ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ አስታወቀ።

ኢንተርፕራይዞች ምርታቸው የሚያስተዋውቁበትና የሚሸጡበት ለ4 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ባዛርና ኢግዚቢሽን በወልቂጤ ከተማ በይፉ ተከፈተ።

የጉራጌ ዞን ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ የስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት ጉባኤ ዛሬ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል እንደገለጹት ስራ የሚፈጠርላቸው ወጣቶች ከልየታ ጀምሮ እስከ ገበያ ትስስር ድረስ የፍትሀዊነት ችግር ካለ ለዘርፉ ውጤታማነት እጅግ ፈተና በመሆኑ ይህንን ችግር መቀረፍ እንዳለበት አመላክቷል።

የወጣቶች የስራ እድል ችግር የሆነው የስራ ተነሳሽነት ችግር ነው ያሉት አቶ መሀመድ ይህንን አመለካከት በማስተካከልና ለኢንተርፕራይዞች የሚፈልጉት መሰረተ ልማት እንዲሟላላቸው መክረዋል።

ለዚህ ዘርፍ ትልቁ ሀብት መሬት ነው ያሉት አቶ መሀመድ በኢንቨስትመንት ሳይለሙ ያሉና የውል መሬቶች እንዲሁም የማእድን ቦታዎች ለወጣቶች መስጠት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

አክለውም ወጣቱ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ለይቶ በማደራጀት ፈትሀዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል።

በየ ጊዜው የሚከናወኑ የወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ ስራ የምክር ቤት አስፈጻሚ አካላት የስራው ተፈጻሚነት መከታተልና መገምገም ይኖርባቸዋል ሲሉ አቶ መሀመድ ተናግሯል።

የጉራጌ ዞን ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አበበ አመርጋ በበኩላቸው በዞኑ ያሉ ስራ አጥ ወጣቶች አደራጅቶ ስራ በመፍጠር ለኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለመሆን ሞዴል ኢንተርፕራይዞች ምርታቸው ለማስተዋወቅና የገበያ እድል ለመፍጠር ባዛሮች የመክፈትና መሰል ተግባራት እየተከናወኑ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

እንዲህ አይነት መድረኮች ለማመቻችትና ለስራ እድል ፈጠራ ተግባር ውጤታማነት የስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤቶች ሚና የጎላ በመሆኑ ሊሰራበት ይገባል ነው ያሉት።

አቶ አበበ አክለውም አስካሁን በከተማና በገጠር እንዲሁም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለ35ሺ 898 ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩ አብራርተዋል።

ዘርፉ ውጤታማ ለማድረግ ቀጣይ የመሬትና የብድር አቅርቦት ችግር በመቅረፍ፣ከአሰራር ውጪ የተያዙ ሼዶች በማስለቀቅ፣ የተፈጥሮ ማዕድናት መነሻ ቁጠባ ለሌላቸው ወጣቶች እንዲሰጥ አቶ አበበ አሳስበዋል።

በብድር አመላለስ ፣ብድር አቅርቦት፣የሼድና የመሬት አቅርቦት፣ የከተማ ምግብ ዋስትና ስራዎች፣የኦዲት አገልግሎት ክንውን፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና በሌሎችም ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

ወጣት ቸርነት ጥላሁን፣ ወጣት ጀሚላ ሰይፉና ወጣት አህመዲን ተሰማ የለቱ ተሸላሚ ኢንተርፕራይዞች ሲሆኑ በአመረቱዋቸው ምርቶች ጥራትና ውጤት ተሸላሚ መሆናቸው ገልጸዋል።

አስተያየት ሰጪዎቹ አክለውም በተከፈተው ኢግዚቢሽንና ባዛር ተሳታፊ ሲሆኑ እንዲህ አይነት ፕሮግራሞች መዘጋጀታቸውን ኢንተርፕራይዞች ልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት እና የገበያ እድል ለመፍጠር አስተዋጽኦ ያበረክታል ሲሉ ተናግሯል።

የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ በሚሰሩበት አካባቢ መሰረተ ልማት እንዲሟላላቸውና መሰል ባዛርና ኢግዚቢሽኖች ወቅቱ ጠብቆ ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

በለቱም በገጠርና በከተማ እንዲሁም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አበረታች ውጤት ላመጡ ኢንተርፕራይዞች የዋንጫ፣የሜዳለያ እና የሰርተፍኬት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነው።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36C

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *