ወጣቱ ማህበረሰብ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በፖለቲካው ዘርፎች ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች ኃላፊነት ውስደው መስራት እንዳለባቸው የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ፡፡

መምሪያው የወጣቶች የማካተት መመሪያ ወይም ጋይድ ላይን ከየሴክተር መስሪያ ቤቶች ለተውጣጡ ባለሙያዎች በዛሬው እለት በወልቂጤ ከተማ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ም/ኃላፊና የወጣቶች ዘርፍ ዋና ኃላፊ አቶ አብዶ ድንቁ ስልጠናውን አስመልክተው እንደገለጹት የወጣቶች ማካተት ጉዳይ ጋይድ ላይን ወይም መመሪያ ላይ የጋራ ግንዛቤ ፈጥሮ ወጣቶችን በማህበራዊ፣በኢኮኖሚያው እና በፖለቲካው ዘርፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች እቅድና በጀት መያዝ እንዳለባቸውና ሁሉም በቅንጅት መስራት እደሚገባ አብራርተዋል፡፡

አቶ አብዱ አክለውም ወጣቱ ባመጣውና እያስቀጠለው ባለው ሀገራዊ ለውጥ በቀጣይም እንዲጠቀም መንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የስራ እድል መፍጠርና ማመቻቸት እንዳለባቸውና በተጨማሪም ከስራ ዕድል ፈጠራና ከኢንተርፕራይዞች ውጭ ያሉ የመንግስት መስሪያ ቤቶችም የወጣቶች ጉዳይ ሊያሳስባቸውና ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

ከዚህ በፊት የነበረው የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ እንዲሰማሩ የተመቻቸው ብድርም አመላለሱ ላይ ብዙ ክፍተቶችና ውስንነቶች በመቅርፍ ዘርፉን ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የወጣት ማዕከላትን ከማጠናከር አንጻርና የወጣቶች በመልካም ስነ ምግባር እንዲታነጽ በወረዳና ከተማ አስተዳድሮች ያለውን ችግሮች በመለየት ከዞኑ መንግስት፣ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ና ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

የጉራጌ ዞን ወጣቶች ሊግ ኃላፊ አቶ ረቢል ከድር በበኩላቸው በቀጣይ በወጣቱ አመለካከት ላይ መስራት እና ከተቋማት በተጨማሪ ወጣቱ የስራ ፈጣሪነት ስሜት ሊኖረው እንደሚገባና ከመንግስት ጋር ቀርቦ በጋራ መስራት እንዳለበት ተናግረዋል ፡፡

አያይዘውም እንደ ሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ወጣቱ ስራ ፈላጊ ብቻ ሳይሆን ስራ ፈጣሪም በመሆን ለሀገር አልኝታ መሆን ይኖርበታል ብለዋል፡፡

አንዳንድ የስልጠናው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ወጣቱን በሁሉም የስራ ዘርፎች ተሳታፊ ና ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግና ሀገራዊ ስሜት እንዲኖራቸው ሁሉም የመንግስት ሴክተር መስሪያ ቤቶች በእቅድና በበጀት ሊደግፉት ይገባል ብለዋል።

አክለውም አስተያየት ሰጪዎቹ የወጣቶች የማካተት መመሪያ ወይም ጋይድ ላይን መሰረት በቀጣይ የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *