ወደ አረብ ሀገር በህጋዊ መንገድ ሄደዉ ስራ እንዲሰሩና መንግስት ተገቢዉን ክትትልና ድጋፍ እንዲያደርግላቸዉ የስራና ከህሎት ሚኒስቴር የፈጠረዉ ምቹ ሁኔታ የበለጠ ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸዉ በወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሙያ ስልጠና የወሰዱ ሴቶች አስታወቁ።

ለስራ ወደ ተለያዩ ሀገሮች የሚጓዙ ሴቶችን የሙያ ስልጠና በመስጠትና በማብቃት ዉጤታማ ስራ እንዲሰሩ ለማድረግ አጽእኖት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነም ተጠቁሟል።

በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች የተዉጣጡ ከአንድ መቶ በላይ ሴቶች ወደ ሳዉድ አረቢያ እንዲሄዱ በኮሌጁ የሙያ ስልጠና እየሰጣቸዉ ነዉ።

የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሀይሩ አህመዲን እንዳሉት መንግስት በሀገር ዉስጥና በዉጭ ሀገሮች ያሉትን የስራ አማራጮችን በመጠቀም ለዜጎች የስራ ዕድል እያመቻቸ ይገኛል።

ዜጎች ተገቢዉን ሙያ ቀስመዉ በሚሄዱበት ሀገር ሁሉ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና እንዲከበሩ እንዲሁም በለፉት ልክ ክፍያ እንዲያገኙ ለማድረግ መንግስት ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሆነም አስታዉቀዉ።

ቀደም ሲል በየብስ፣ በባህርና በአየርም መድረሻቸዉም ሳያዉቁ ዜጎች በህገወጥ መንገድ ሲሰደዱ እንደነበረምና የልፋታቸዉ እንደማያገኙና የተለያዩ ችግሮች ይደርስባቸዉ እንደነበረም አስታዉሰዋል።

ይህንንም ችግር ለመቅረፍ የፌዴራል ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተለያዩ ሀገራቶች ጋር ዜጎች የስራ ዕድል እንዲያገኙ ህጋዊ በሀኒንገድ እንዲሄዱ መስመር በመዘርጋት ከሀገራት ጋር ስምምነት ተፈራርሞ እንቅስቃሴ ጀምሯል ብለዋል።

በዚህም የሳዉድ አረቢያ መንግስት ወደ 5 መቶ ሺህ የሚጠጉ ዜጎችን ለስራ እልጋለሁ ብሎ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በሀገሪቱ ባሉ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ሰልጥነዉ ህጋዊ በሆነ መንገድ ሄደዉ እንደ ሰዉ እንዲከበሩና የሚያገኙትም ገንዘብ የተሻለ እንዲሆን በቅንጅት እየተሰራ ነዉ ብለዋል።

ከ100 በላይ ሰልጣኝ ሴቶች በዚኛዉ ዙር ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን በቀጣይም ሌሎች ሴቶችና ወንዶችን ተጠቃሚ እንደሚሆኑም አመላክተዉ ስልጠናዉ የወሰዱ ሴቶችም መጋቢት 26/2015 ዓመተ ምህረት በረራ የሚያደርጉም መሆኑም አስረድተዋል።

ለስራ ወደ ተለያዩ ሀገሮች የሚጓዙ ሰዎችን አሰልጥኖ በማብቃት እያስመዘነ እንደሚገኝ የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ገልጻል፡፡

ኢትዮጵያዊያን ሰራተኞች በውጪ ሃገር የሥራ ስምሪት በህጋዊ መንገድ ተቀጥረው ለመስራት የሚችሉባቸው ሃገራት ከሀገራችን ጋር ውል በመግባት እየተሰራ ይገኛል፡፡

የጉራጌ ዞን አስተዳደር አማካሪ አቶ ፈቱ አብዶ እንዳሉት ሀገሪቱ የገባችውን ውል መነሻ በማድረግ ሰዎች ሰብአዊ መብታቸው ተጠብቆ በህጋዊ መንገድ ወደ ተለያዩ ሀገሮች ሄደው ውጤታማ እንዲሆኑ ዞኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑም አመላክተዋል።

ቀደም ሲል ሴት ልጆች በደላላና በህገወጥ መንገድ ሄደዉ ለከፍተኛ እንግልትና ስቃይ ይዳረጉ እንደነበረና ይህንን ለማስቀረት የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ካሪኩለም በመቅረጽ ወደ አረብ ሀገር ለሚሄዱ ሴቶች በወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሙያ ስልጠና መዉሰዳቸዉ በስራቸዉ ዉጤታማ ያደርጋቸዋል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ሀላፊ ወይዘሮ አመተረዉፍ ሁሴን እንዳሉት በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች ህገወጥ የሰዎች ዝውውር እንዲቀንስ ለማህበረሰቡ የተለያዩ ግንዛቤዎችን በመስጠትና ህገወጥ ደላሎች እንዳይኖሩ እየተሰራ ይገኛል።

ሴቶች በህጋዊ መንገድ አረብ ሀገር መሄዳቸው አላማቸውን ከማሳካት አልፎ ለሀገርም እድገት ትልቅ አስተዋጾ ያበረክታል ብለዋል፡፡

ስልጠና ሲሰጥ ያገኘዉ በወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሆቴልና ቱሪዝም አሰልጣኝ አቶ ምህረተአብ እንዳለዉ በኮሌጁ ወደ አረብ ሀገር የሚሄዱ ሴቶችን እያሰለጠነና በስራቸዉ ብቁ እንዲሆኑ እየሰራ ይገኛል።

በሚሰሩበት ቤት ነጻነታቸዉን አጥተዉ በደላላ የሰሩትን ገንዘብ ይወሰድባቸዉ እንደነበረና አንዲሁም ህይወታቸዉም የሚያጡ እንደነበሩም አስታዉሶ ይህንንም ለማስቀረት የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሚሄዱበት ሀገር ጋር አግሪመንት ተፈጠሮ እየተሰራ ነዉ።

ወደ አረብ ሀገር ለመሄድ በኮሌጁ ስልጠና እየወሰዱ የነበሩ አንዳንድ አስተያየት የሰጡን ሴቶች እንዳሉት ቀደም ሲል ሴት እህቶቻቸዉና ወንድሞቻቸዉ ህጋዊ ሆነዉ ባለመሄዳቸዉ ከቤት ወጥተዉ የቀሩት መንግስት በህጋዊ መንገድ ሳይልካቸዉ በመቅረቱ እንደሆነም አስታዉሰዋል።

በመጨረሻም ይህንን ምቹ ሁኔታ ያመቻቸዉን የስራና ክህሎት ሚኒስቴርን አመሰግነዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *