ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በዩኒቨርሲቲ- ኢንዱስትሪ ትስስር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተፈራርመዋል።

የትምህርት ሚኒስትር የተቋማት ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዴስክ ኃላፊ አቶ ተሾመ ዳንኤል ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከኢንዱስትሪ ጋር በትስስር ቢሰራም በዘርፉ የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት አልተቻለም።

ይህንን ለመቀየር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከኢንዱስትሪው ጋር በመቀናጀት ችግር ፈቺ ውጤታማ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል በመክፈቻ ንግግራቸው ዩኒቨርሲቲዎች ከኢንዱስትሪ ጋር በመተሳሰር ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር ከማድረግ ባለፈ ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪ ለመገንባት ሚናው ከፍተኛ ነው።

አክለውም ኢንዱስትሪው ብቁ የሰው ሀይል ለሟሟላት፣ ችግር ፈቺ ምርምር ለማካሄድና ቴክኖሎጂ በማመንጨት ሁለንተናዊ ስኬት ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋልም ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስር አስፈላጊነት ዩኒቨርሲቲው የምርምር እና ትምህርት ፕሮግራሞቻቸው ከኢንዱስትሪ ፍላጎት ጋር እንዲያቀናጁ ያስችላቸዋል ብለዋል።

ከዚህም ባለፈ ከኢንደስትሪ ጋር በመተባበር የቴክኖሎጂ ፈጠራን ከማሳደግ ባለፈ ዩኒቨርሲቲዎች የምርምር ግኝቶቻቸውና እውቀቶቻቸው ለኢንዱስትሪው አጋሮች በብቃት እንዲያስተላልፉ ያደርጋልም ነው ያሉት።

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የኢንዱስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበበ ያበኬር ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የጋራ ምርምር በመስራት ብቁ ተማሪዎች ለማፍራት ያስችላል ብለዋል።

ኢንዱስትሪዎች ከዩኒቨርሲቲው በጋራ መስራታቸው ተቋማት ያላቸውን አቅም በማቀናጀት ለመጠቀምና ዩኒቨርሲቲው ለተማሪዎችና መምህራን የተግባር እውቀት እንዲያገኙ ያደርጋል ብለዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አምዶ በበኩላቸው ትስስሩ ብቁና ስራ ፈጣሪ ዜጋን ለማፍራት ሚናው የላቀ ነው ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ የዩንቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስሩ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የፈጠራ ስራዎች ተሰርተው ለተጠቃሚ ተደራሽ እንዲሆኑ የግብ ስምምነት መፈራረማቸውን ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው የተማረ ብቁ የሰው ሀይል ለማፍራት ኢንዱስትሪዎች የፈጠራ ስራ ባለቤቶችን የእውቅት ሽግግር እንዲያደርጉ ባለሙያዎቻቸው ወደ ዩኒቨርሲቲው መላክ እንዳለባቸው ገልጸው ለዚህ ውጤታማነት በቅንጅት በትኩረት መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ከዩኒቨርስቲው ባለፈ ከባለሀብቶች ጋር በማስተሳሰር የፈጠራ ስራዎች ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉና የፈጠራ ባለቤቶች በፈጠራ ሀሳባቸው ብዙም ኢንዱስትሪዎች ባወጡት ገንዘብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል ብለዋል።

በምክክር መድረኩም የክልል፣ የዞኖችና የልዩ ወረዳ የሚመለከታቸው አካላት የተገኙ ሲሆን የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር ከ13 የግልና የመንግስት ተቋማት በጋራ ለመስራት የግብ ስምምነት ተፈራርመዋል ሲል የዘገበው የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *