ከ8 መቶ በላይ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር መቻሉ በጉራጌ ዞን የቡታጅራ ከተማ የደስታ ጋርመንትና ቴክስታይል ፋክተሪ ገለፀ።

ፉክተሪ በጋርመንትና ቴክስታይል ዘርፍ በሀገራችን ካሉ ኢንድስትሪዎች ቀዳሚ ሆኖ እንዲገኝ በትጋት ይሰራል ተባለ።

ድርጅቱ እያከናወነ ያለው የስራ እንቅስቃሴ በቡታጀራ ከተማ ስልጠና እየወሰዱ ያሉ የክልልና የተለያዩ ዞኖች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በትላንትናው ፋክተሪው ጎብኝተዋል ።

ግንባታው በ30ሺ ካሬ መሬት ስፋት ላይ ተሰርቶ በ2011 አመተ ምህረት ስራ መጀመሩ የደስታ ጋርመንት ፉክቶሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ስራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ ወልዴ ተናግረዋል።

ኩባንያው ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፣ኢንተርፕራይዞችና አጋር ድርጅቶች በጋራ በመሆን እየሰራ እንደሆነ ስራስኪጁ ገልፀዋል።

ደስታ ጋርመንት በዞኑ በአምራች ዘርፍ ብቸኛው ግዙፍ ኢንቨስትመንት በመሆኑ ለየት ያደርገዋል።

መቀመጫው ቡታጅራ አድርጎ ለመላ ጉራጌ ዞን አገልግሎት የሚሰጠው ደስታ ጨርቃጨርቅ ለዞኑ ኢንድስትሪ ፈር ቀዳጅና በኢንድስትሪው ዘርፍ እንደ ሀገርም የበኩሉን እየተወጣ መሆኑ ስራስኪያጁ ገልፀዋል።

በተጨማሪም ወጣት አምራች ሀይሉን በመጠቀም የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በማሳደጉ እረገድም የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሆነ በፋብሪካው የስራ እድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች ምስክር ናቸው።

አቶ ያሬድ እንደሚሉት የሚሰሩ የልብስ ስራዎች 90 ከመቶ ለውጭ ሀገር የሚላኩ ሲሆን በዚህም ሀገሪቱ የምታገኘው ገቢ ከፍ እንዲል ያደርገዋል።

ብራንድ ትሸርቶች፤ የስፖርት ትጥቆችና ልዩ ልዩ የጨርቅ ልብስ ውጤቶች ያመርታል ይላሉ አቶ ያሬድ ወልዴ።

አቶ ያሬድ ወጣቱ በስራ እጦት ምክንያት ከሀገር እንዳይሰደድ፣በሱስ እንዳይጠመድ፣ አልባሌ ቦታ እንዳይውል በማድረግ እራሱና ሀገሩን እንዲጠቅም አድርጓል።

በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ለከተማው ብዙ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ መሆኑና ለሆስፒታል፣ ለትምህርት ቤት የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፍና ጥገና እንደሚያደርግም ስራስኪያጁ ገልፀዋል።

በደስታ ጋርመንት ውስጥ ሲሰሩ ያገኘናቸው ወጣቶች እንደተናገሩት ከዛ በፊት ያለስራ በመቅረታችን ለስደትና ለሌሎች ችግሮች ተጋላጭ ሆነው እንደነበር ዛሬም ድረስ አንረሳውም ይላሉ።

ሆኖም ግን ወደ ደስታ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ከመጡ በኋላ ከተረጂነት ወደ እረጂነት በመቀየራቸው ደስታችን ወደር የለሽ ነው ሲሉ ይመሰክራሉ።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል በዚህ ወቅት እንደገለፁት ካምፓኒው ለዞኑ ብሎም ለሀገር የሚሰጠው አገልግሎት እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ገልጸዋል።

በተለይም በወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ የሚሰጠው አገልግሎት ቀዳሚው ሲሆን ቀጣይ የተለያዩ ስራዎችን በጀመረ ቁጥር የሚሰጠው አገልግሎት ስለሚጨምር መንግስት ደግሞ ለድርጅቱ አስፈላጊው የሆነ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አሳውቀዋል።

በጉብኝቱ የደቡብ ክልል ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ጥላሁን ከበደ፣የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል፣የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ክፍሌ ለማ ጨምሮ ከክልሉ ከተለያየ ቦታ የመጡ የዞን ከፍተኛ አመራሮች ተገኝቸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው ።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *