ከ3 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተለያዩ አልባሳት፣ፍራሽ ፣የንጽህና መጠበቂያ ፣የትምህርት መማሪያ መጽሀፍና መሰል ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጉም የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር አስታወቀ።

ቁሳቁሱም በዞኑ በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ መስተዳደሮች ለሚገኙ ለአረጋዉያን ፣ ለተጋላጭ ወገኖችና ለህጻናቶች ድጋፍ ተደርጓል።

የጉራጌ ብሔረሰብ ባህል ቋንቋና አንድነት እንዲጠናከር አጽዕኖት ሰጥቶ እየሰራ አንደሆነም ተጠቁሟል።

የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ዋና ዳይረክተር አቶ ቅባቱ ተሰማ እንዳሉት የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች እያከናወነ ይገኛል።

ማህበሩ ከተወላጁ ማህበረሰብ ፣ረጂ ድርጅቶችና መንግስትን በማስተባበር በአካባቢዉ የተለያዩ የልማት ስራዎችና የብሔረሰቡ ባህል ቋንቋና አንድነት እንዲጠናከር አጽዕኖት ሰጥቶ እየሰራ አንደሆነም አብራርተዋል።

በዘንድሮ ክረምት የምግብ ቁሳቁሶች ለተቸገሩ ወገኖች ድጋፍ በማድረግና እንዲሁም ወልቂጤ ከተማ ለሚገኙ አረጋዉያን የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጋቸዉም አስታዉሰዉ እንዲሁም ሰሞኑ በዞኑ የአረጋዉያን በአል ላይ ለየት ባለ መልኩግምታቸዉ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ብርድ ልብስ፣ፍራሽና ለሌሎች ቁሳቁሶችና ለተቸገሩ ተማሪዎች የሚሆን መጽሀፍ ፣ ደብተር ፣ እስክሪፕቶችና መሰል ቁሳቁሶች በመግዛት ድጋፍ ማድረጋቸዉም አብራርተዋል።

ይህንም ድጋፍ በአዲስ አበባ ያሉ የብሔረሰቡ ተወላጆችና የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ከፍተኛ ድጋፍና ትብብር አድርገዋል ያሉት አቶ ቅባቱ በቀጣይም ልማትና ባህል ማህበሩ መሰል ስራዎች ላይ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ተጠናክሮ እንደሚሰራም አብራርተዋል።

በገጠር በንጹህ መጠጥ ዉሃ ፣በትምህርትና በጤና ላይ በመስራት አረጋዉያንና ለተለያዩ ችግር የተጋለጡ ወገኖችን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም አስታዉቀዋል።

የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር የጀመረዉን የልማት ስራ ዉጤታማ እንዲሆን የብሔረሰቡ ተወላጆችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የልማትና የባህል ማህበሩ አባል በመሆንና ጠጋ ብሎ በማየት እንዲሁም በመጠየቅ የማህበሩ ተባባሪና አጋዥ መሆን አለባቸዉ ብለዋል።

የመንግስት አካላቶች ህብረተሰቡን በማስተባበርና ሌሎች የልማት ስራዎች በማገዝ ልማት ማህበሩን በማጠናከር መንግስታዊ ሚናቸው አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ከመንግስት ሴክተር መስሪያ ቤቶችና ከሌሎችም አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የበለጠ ተቀራርቦ በመስራት ማህበረሰቡ ለአንድነቱና ለታሪኩ ፣ለባህሉና ለቋንቋዉ እንዲሁም ለልማት በማስተባበር የተጀመረዉን መልካም ጅምር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አብራርተዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *