ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የሚዉል የበሶ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ የወልቂጤ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በከተማዉ ለ5ኛ ዙር በግንባር እየተዋደቀ ላለዉ የሰራዊት አባላት በሶ አሽጎ ለመላክ እየሰሩ እንደሆነም አንዳንድ የከተማው ሴቶች አስታዉቀል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ሄኖክ አብድልሰመድ እንደገለፁት የከተማዉ ህዝብና መንግስት እስከ አሁን ከ8 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የእርድ ሰንጋ ፣በጥሬ ገንዘብና ደረቅ ምግብ በማዘጋጀት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አለኝታነታቸዉን አሳይተዋል።

አሁን ላይ ለአምስተኛ ጊዜ ለሀገር ህልዉና እየተዋደቀ ላለዉ ሰራዊት ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የበሶ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን ለዚህም ዝግጅት በከተማዉ የሚገኙ ሴቶች ጠዋት አስራ ሁለት ሰአት ወጥተዉ ገብስ አስፈጭተዉ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በሶ እያዘጋጁ እንደሆነም አብራርተዋል።

የከተማዉ ነጋዴ፣ባለሀብትና መላዉ የህብረተሰብ ክፍሎች ፣ የመንግስት ሰራተኞችና ወጣቶች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እያደረጉት ላለዉን ከፍተኛ ድጋፍም ከልብ አመስግነዋል።

በከተማዉ የዘማች ቤተሰቦች በተለያዩ መንገዶች ለመርዳት ጥረት እየተደረገ እንደሆነም አስረድተዉ የህልዉና ጦርነት እስኪጠናቀቅ ድረስ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚያደርጉት ድጋፍም አጠናክረው የሚቀጥሉ እንደሆነም አስረድተዋል።

የወልቂጤ ከተማ ሴቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ሰላም ፍቃዱ በበኩላቸዉ በከተማዉ ከሁሉም ክፍለ ከተማ የተዉጣጡ ሴቶች በተለያዩ ጊዜያት ለመከላከያ ሰራዊት የሚሆን ስንቅ የማዘጋጀት ስራም እየሰሩም እንደሆነም አስታዉቀዋል።

አሁን ደግሞ ለ5ኛ ጊዜ ለሚደረገዉ የበሶ ድጋፍ ሴቶች ከማስፈጨት እስከ ማሽግ ድረስ በራሳቸዉ ተነሳሽነት ስራ እየሰሩ እንደሆነም አስታዉቀዋል።

የበሶ ዝግጅት ሲያደርጉ ያነጋገርናቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት ከሀገር የሚበልጥብን ምንም ነገር የለም በማለት የሀገራችን ከዉስጥና ከዉጭ ጠላቶችን ለማዳን ህይወቱን ለመገበር ግንባር እየተፋለመ ላለዉ ሰራዊት በገንዘብ በጉልበትም የሚያደርጉ አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉም አስረድተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው ።

  • አካባቢህን ጠብቅ!
  • ወደ ግንባር ዝመት!
  • መከላከያን ደግፍ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *