ወልቂጤ ከተማ ለ2017 የውድድር ዘመን የክለብ ላይሰንሲንግ ምዝገባ እና ሌሎች የተቀመጡ መስፈርቶችን ባለማሟላቱ ከፕሪሚየር ሊጉ መሰረዙ ይታወሳል፡፡
ክለቡ የውድድር ፈቃድ መስፈርቶችን እንዲያሟላ በተሰጠው ጊዜ መሰረት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር የሚጠይቀውን መስፈርት በማሟላቱ በከፍተኛ ሊግ እንዲጫዎት መደረጉ ተመላክቷል፡፡
በዚህም መሠረት ወልቂጤ ከተማ በ2017 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ ላይ ተደልድሎ የሚወዳደር ይሆናል።
FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)