ከ112 ሚሊየን ብር በላይ በበጋው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ገለፀ።

የጉራጌ ዞን የበጎ ፍቃድ አገልግሎት አብይ ኮሚቴ የበጋው ወራት የበጎ ፈቃድ ስራዎች አፈፃፀም ዛሬ ገምግመዋል።

የጉራጌ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪና የበጎፈቃድ አገልግሎት አብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል እንደገለፁት የበጎ ፈቃድ ስራዎች በዞናችን በርካታ ችግር ውስጥ የገቡ ቤተሰቦች ችግር እየፈታ ያለ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ ተግባር ነው።

የበጎ ፈቃድ ስራ ከምንም በላይ በበርካታ ችግር ውስጥ ያሉና ረዳትና ጠዋሪ የሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የምንታደግበት ሲሆን በተጨባጭ በዞናችን ስኬታማና ለህሊና እረፍት የሚሰጡ ሰራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።

እስካሁን በተገኙ ውጤቶች የባለሀብቱና የወጣቶች ተሳትፎ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ያመላከቱት አቶ አለማየሁ በቀጣይም ተሳትፏቸው ለማሳደግ በየደረጃው ያሉ አብይና ቴክኒክ ኮሚቴ ከወጣቱና ከባለሀብቱ የበለጠ ተቀራርቦ መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል።

በቀጣይ ቀሪ ወራት በየአካባቢው መሰረታዊ የመጠለያ ችግር ያለባቸውና የተቸገሩ ማህበረሰብ ክፍሎች ቤት በመስራትና በመጠገን፣ለትምህርት ጥራቱ መሻሻል አጋዥ ስራዎች በመስራት፣የወጣቶች ስብእና ግንባታ ስራዎች በማጠናከር፣ በሰላም እሴት ግንባታ፣ የወጣቶች መዝናኛ ቦታዎች በማሻሻልና በሌሎችም ዘርፎች በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትል ሀላፊና የወጣቶች ዘርፍ ሀላፊ አቶ አብዱ ድንቁ የባለፉት ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት በጋው ወራት በተሰሩ ስራዎች 212 ሺህ 211 የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ በማድረግ 112 ሚሊየን 011 ሺህ 033 ብር ግምት ያለው ስራ በጥሬ ገንዘብ፣በጉልበት፣በቁሳቁስና በሌሎችም ዘርፎች መስራት ተችለዋል።

የዞኑ ወጣቶች ባለፉት አመታት በተለይም በክረምት ወራት በርካታ አስተማሪና እንደ ክልልም አርአያነት ያለው ስራ መስራታቸው አስታውሰው በተለይም ሀገራችን በገጠማት የህልውና ዘመቻ የከፈሉት ሁሉ አቀፍ መሰዋአትነት ሁሌም የሚዘከር ነው ብለዋል።

ይህ በክረምት ብቻ ሲሰራ የነበረው የበጎ ፈቃድ ስራ በበጋውም በማጠናከር በዞኑ የተቸገሩት ቤት በመጠገንና እርሻ በማረስ፣ የዘማች ቤተሰብ በመርዳት፣ በደም ልገሳ፣በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች፣በአካባቢ ሰራዊት ስልጠና በመውሰድ ሰላም በማስጠበቅ፣በፅዳትና ውበት ስራዎች፣የመንገድ ደህንነት ስራዎች በመስራትና በሌሎችም 14 ዘርፎች ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ መሆኑ ተናግረዋል።

በነዚህ ስራዎች እስካሁን 121 ሺህ 891 ወጣቶችና በጎፈቃደኛ የህብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸው ገልፀው በቀጣይም የበጎ ፈቃድ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጠይቀዋል።

ኮሚቴው የቀረበው ሪፖርት ዝርዝር ግምገማ ያካሄደ ሲሆን በቀጣይ ወራት የተሻለ እና ውጤታማ ስራ ለመስራት የመፍትሄ አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *