ከፍተኛ ፍክክር የታየበት የወልቂጤና የቸሃ ወረዳ እግር ኳስ የፍጻሜ ዉድድር በመለያ ምት 5ለ4 በሆነ ዉጤት በቸሃ ወረዳ አሸናፊነት ተጠናቋል።

የጉራጌ ዞን የልዩ ልዩ ስፐርታዊ ዉድድርና 21ኛ የባህል ስፖርቶች ዛሬ ፍጻሜዉን አግኝቷል።

ለ 9 ተከታታይ ቀናት በወልቂጤ ከተማ ሲካሄድ የነበረዉ የልዩ ልዩ ሰፖርቶች ዉድድርና 21ኛ የባህል ስፖርት ዉድድር ዛሬ ፍጻሜዉን አግኝቷል።

በፈጻሜ ዉድድር መዝጊያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን ምክትል አሰተዳዳሪ አቶ አበራ ወንድሙ እንዳሉት ዞናዉ የልዩ ልዩ ስፖርት ሻምፒዮና ዉድድር በአትሌቲክስ ፣በእግር ኳስ ፣ በቮሊቮል ፣ በወርልድ ቴኳንዶ ፣ በባህል ሰፖርቶች ፣ በፓራሊፒክስ የዉድድር አይነቶች ተተኪ ስፖርተኞች የታዩበት ዉድድር ነበር ብለዋል።

ስፖርት ኢኮኖሚያዊ ፣ፖለቲካዊ እንዲሁም ማህበራዊ ፋይዳዉ የጎላ እንደሆነም ተናግረዉ ስፖርት በባህሪዉ ዘርን ቀለምን፣ ሀይማኖትን የማይለይ እና በጋራ የሚደረጉ ዉድድር ከመሆኑም ባሻገር ዞናዊ አንድነት በማጠናከር ረገድ ፋይዳዉ የጎላ እንደነበረም አመላክተዋል።

በወልቂጤ ከተማ ይህ ዉድድር በመደረጉ ትልቅ መነቃቃት የፈጠረ እንደሆነም ተናግረዉ አንዱ የስፖርት ገጽታዉ በኢኮኖሚ ዘርፍ የሚያመጣዉ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እንዳለና በከተማዉ ደሰጃ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዉ እንቅስቃሴም ፈጥሮ እንደነበረም ተናግረዋል።

በዚህ ዉድድር ምንም አየነት ከሽታ ሳይፈጠር ከደጋፊ እስከ እስከ ስፖርተኘች ያሳየት ስፐርታዊ ጨዋነት የሚደነቅም እንደሆነም አመስግነዋል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ፈይሰል ሀሰን የልዩ ልዩ ሰፖርት ሻምፒናና 21ኛዉ የባህል ስፖርቶች መዝጊያ ፕሮግራም ላይ ተገኝተዉ እንዳሉት ለ9ኝ ተከታታይ ቀናት በ6 የስፖርት አይነቶች ዉድድር ሲደረግ መቆየቱም አስታዉሰዉ ይህንንም ዉድድር በዛሬ ዕለት በእግር ኳስ ዉድድር ፍጻሜ አግኝቷል ብለዋል።

ቸሃ ወረዳ ከወልቂጤ ከተማ ጋር ባደረጉት የፍጻሜ ዉድድሮ ከፍተኛ ፉክክር የታየበትና በቸሃ ወረዳ አሸናፊነትም መጠናቀቁም አመላክተዋል።

ዘንደሮ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ያለምንም ኮሽታ ሁሉመ ዉድድሮች በሰላም ተጠናቀዋል ብለዉ በስፖርተኞችና በደጋፊዎችም ዘንድ ፍጹም ዲሲፒሊን የተስተዋለበት ዉድድርም እንደሆነም አመላክተዋል።

በሁሉም የስፖርት አይነቶች ዞኑን ወክለዉ የሚሳተፉ ስፖርተኞች የተመለመለበት እንደሆነም ተናግረዉ ዳኞች ፣አሰልጠኞች ፣መላዉ ስፖርተኞች ፣ አቅማቸዉ የፈተሹበት እንደሆነም ተናግረዉ ዉድድሩም ለሀገሪቱ ተተኪ ሰፖርተኞች ያፈራንበት ነዉ ብለዋል።

ዉድድሮችም የዞኑ መልካም ገጽታ የተገነባበት ከመሆኑም ባሻገር አንድነታችን ያጠናከርንበትም እንደሆነም አብራርተዋል።

ወንድማማችንትን የተስተዋለበት የወልቂጤና የቸሃ ወረዳ እግር ኳስ የፍጻሜ ዉድድር ደጋፊዉ ትልቅ ዉበት ሁነዉት ዉለዋል።

       በእግር ኳስ ስፖርት 

ኮከብ ተጫዎች

#ግሩም ዳንኤል ከቸሃ ወረዳ

ኮከብ በረኛ ሙሉቀን ተሰማ ከወልቂጤ ከተማ አስተዳደር

የወርቅ ሜዳሊያና የዋንጫ ተሸላሚ

የቸሃ ወረዳ

የብር ሜዳሊያ
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር

የነሀስ ተሸላሚ
የእምድብር ከተማ አስተዳደር

@ በአትሌቲክስ ዉድድር ከ1 እስከ 3 የወጡ ወረዳዎች !!

          1ኛ የጌታ ወረዳ ( የወርቅ ሜዳሊያና ዋንጫ) 

           2ኛ ጉመር ወረዳ (የብር ሜዳሊያ )

           3ኛ  ቸሃ ወረዳ  (የነሀስ ሜዳሊያ)

በቮሊ ቮል ዉድድር ከ1 እስከ 3 የወጡ ወረዳዎች

        1ኛ የአበሽጌ ወረዳ 

         2ኛ የገ/ጉ/ወለኔ ወረዳ 

          3ኛ ወልቂጤ 

በሴቶቾ የዋንጫ ተሸላሚ

እንደጋኝ

በባህል ስፖርት ዉድድር ከ1 እስከ 3 የወጡ ወረዳዎች

1ኛ ምሁር አክሊል

2ኛ ቸሃ ወረዳ

3ኛ አበሽጌ ወረዳ

በወርልድ ቴኳንዶ ዉድድር ከ1 እስከ 3 የወጡ ወረዳዎች

1ኛ ጉመር ወረዳ

2ኛ አረቅጥ ከተማ

3ኛ አገና ከተማ

በመጨረሻም ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የፀባይ ዋንጫ ሲበረከትለት ለዳኘች ማህበር ለተለያዩ የስፖርት ፌዴሬሽኖች ፣የለባህል ፣የአትሌቲክስ ፣የእግር ኳስ፣ የቮሊቮል ፌዴሬሽኖች እንዲሁም ለቴክኒክ ኮሚቴዎች፣ ለተለያዩ ሰፖርት ዳኞች ፣ አዉቅናና ሰርተፍኬት ተሰጥቷል ሰል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *