ከፌደራል፣ ከክልልና ከከተማ አስተዳደር የተወጣጡ የወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ስራ አስፈጻሚዎች የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ንቅናቄና የብልፅግና ትሩፋት ለወጣቶች ተጠቃሚነት በሚል በጉራጌ ዞን ከእምድብር ከተማ አስተዳደርና ከቸሃ ወረዳ ወጣቶች ጋር የልምድ ልውውጥ ተካሄደ።


በእለቱም በብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ዋና ጽህፈት ቤት አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ቃል የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመር፣ የችግኝ ተከላ ብሎም የአንዲት አቅመ ደካማ ቤት በአዲስ ለመገንባት የማስጀመርና በከተማው ወጣቶች በሌማት ትሩፋት፣ በገጠርና በከተማ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ተጎብኝቷል።

የኢፌድሪ የብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወጣት ወይዘሪት አባንግ ኩሙዳን እንዳሉት የልምድ ልውውጡ አላማ በጉራጌ ዞን እምድብር ከተማ በወጣቶች በሁሉም ዘርፍ የተከናወኑ ምርጥ ተሞክሮዎችን ወደ ሌሎችም የሀገሪቱ ክፍሎች ለማስፋት ያለመ ነው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲና ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ ነኢማ ሙኒር እንዳሉት በሀገራችን የፖለቲካ፣የኢኮኖሚና የማህበራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ሁለንተናዊ አንቅስቃሴ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ ነው።

በመሆኑም በሀገሪቱም ሆነ በክልሉ በኢኮኖሚው መስክ እየተደረጉ ባሉ አንቅስቃሴዎች የወጣቶች ሚና እንዲጎለብት ሰፊ ስራ መሰራቱን ጠቁመው በዚህም ወጣቶቸ በሁሉም ዘርፍ ተሳትፎአቸው ብሎም ተጠቃሚነታቸው እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ በሁሉም ዘርፍ በወጣቶች ሊግ መሪነት የተጀመሩ የንቅናቄ ተግባራት ላይ በርካታ ወጣቶች በዶሮ እርባታ፣ በወተት፣ በአሳ ሀብት ልማት፣ በምርጥ ዘር ምርት፣ በአረንጓዴ አሻራ፣ በበጋ መስኖ እና በሌሎችም ስራዎች ላይ የወጣቶች አሰተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

እነዚህ ጅምር እንቅስቃሴዎች በማጠናከር በሁሉም ቦታና አማራጮች የወጣቶች ኢኮኖሚ ሊያሻሽሉ የሚችሉ ተግባራትን አጠናክሮ በማስቀጠሉ ሂደት በተለይም የወጣቶች ሊግ አባላት በተደራጀ ሁኔታ በአደረጃጀቶቻቸውን አማካኝነት በቀጣይም በንቃት መስራት ይጠበቅባቸዋል።

የጉራጌ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ በበኩላቸው በዞኑ ወጣቶች በግብርናው ዘርፍ በማሰማራት በተሰራው ስራ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ተችላል።

በበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ በሌማት ትሩፋትና በሌሎችም ዘርፎች እየተሰሩ ያሉ አበረታች ተግባራት በቀጣይም በማጠናከር እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በልምድ ልውውጥ ፕሮግራሙ የኢፌድሪ የፌደራል፣ የክልሉ ብልጽግና ጽህፈት ቤት የወጣቶች ሊግ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዶ ድንቁ፣ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ፣ ከፌደራል፣ ከሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደር የተወጣጡ የወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ስራ አስፈፃሚዎችና የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የእምድብር ከተማ አስተዳደር አመራሮችና የከተማው ወጣቶች ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *