ከጉራጌ ዞን ከሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የመጀመሪያ ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎችን ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሙሉ በሙሉ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማድረሳቸውን የዞኑ ትራንስፖርትና እና መንገድ መምሪያ ገለፀ።

ጥቅምት 3/2015ዓ.ም

ከጉራጌ ዞን ከሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የመጀመሪያ ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎችን ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሙሉ በሙሉ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማድረሳቸውን የዞኑ ትራንስፖርትና እና መንገድ መምሪያ ገለፀ።

የመምሪያው ኃላፊ ወ/ሮ ትብለጥ እስጢፋኖስ እንደገለፁት የፈተና ስርዓቱ ፍፁም ሰላማዊ እና ከእንግልት የፀዳ እንዲሆን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በትጋት ሲሰሩ እንደነበር ገልፀዋል።

በዚህም የፈተና ፕሮግራሙ በታቀደው ቀን ተጠናቆ ተማሪዎችንም በዛሬው እለት ሙሉ በሙሉ ወደየአካባቢያቸው ማድረሳቸውን አሳውቀዋል።

ኃላፊዋ አያይዘውም ለተግባሩ መሳካት ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የትራንስፖርት ማህበራት እና የተሽከርካሪ ባለንብረቶች፣ የትራንስፖርት እና መንገድ ልማት አመራር እና ባለሙያዎች ፣የትምህርት አመራርና ባለሙያዎች ፣የፀጥታ መዋቅር አመራር ና ባለሙያዎች የዞን የወረዳና የከተማ አስተዳደር መዋቅሮች ላደረጉት ንቁ ተሳትፎ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *