ከጀግናው ሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመሰለፍ የሀገር ሉአላዊነት ሲጠብቁ ለተሰው የሰራዊት አባላት ቤተሰብ የመሬት እና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ በጉራጌ ዞን የቸሃ ወረዳ አስተዳደር ገለፀ።

በቸሀ ወረዳ መገናሴ ቀበሌ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ቤተሰቦች 250 ካ.ሜ መሬት እና አምስት ሺህ ብር የቸሀ ወረዳ ዋና አስተዳደር ድጋፍ እንዳደረገላቸው የቸሀ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት አስታወቀ።

የቸሀ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ አድማሱ እንደገለፁት በሀገራችን ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ወራሪው የጁንታው ሀይል የከፈተብን ጥቃት ለመመከት የሚያስችል የሰራዊት ምልመላ በማድረግ መላካችን ይታወቃል።

እንደ ሀገር የተከፈተብን ጥቃት በጋራ ለመወጣትና ለመከላከል የሚያስችል የመከላከያ ሰራዊት አባል በመመልመል፣ስንቅ በማቅረብ እንዲሁም ሌሎችንም ድጋፍ በማድረግ የቆይተናል ብለዋል። በዚህም እንደ ወረዳ ወደ መከላከያ ከተቀላቀሉ ውስጥ ሁለት የመከላከያ አባላት መሰዋታቸው ተናግሯል።

እነዚህ ጀግኖች በሀገር በመጣ ፈተና ላይ ለመከላከልና ሀገራቸው ለመታደግ እንዲሁም የዜጎች ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ የተሰዉ ቢሆንም የነዚህ ጀግኖች ቤተሰብ ለመደገፍ የወረዳው መንግስት የመሬትና የገንዘብ ድጋፍ እንዳደረገም ተናግሯል።

የቸሀ ወረዳ የአስተዳደር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ብሩክ ፍቃዱ እንዳሉት የወረዳው ማህበረሰብ ህይወቱ የሰዋው ላለው ለጀግናው ሀገር መከላከያ ሰራዊት ለዘማች ቤተሰብ የወዠ ቀበሌ ለደገሙ አዴላ ቤተሰብ እና ለመገናሴ ቀበሌ ለሰለሞን ታደሰ ቤተሰብ ለእያንዳንዳቸው 250 ካ.ሜ መሬትና የገንዘብ ድጋፍ መደረጉ ተናግሯል።

በተጨማሪም ከቀበሌ አመራሮች በመነጋገር በበጋ የበጎ አድራጎት ወጣቶ ለሟች ቤተሰብ ጓሮ እንዲታረስላቸው አድርገናል ብሏል።

የቸሀ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙራድ ከድር እንደተናገሩት የወረዳው የበጎ አድራጎት ወጣቶች ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለዘማች ቤተሰብ እያደረጉት ላለው በጎ ስራ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የአከባቢው ወጣቶችን በማሳተፍ ህይወቱን ለሀገር እየሰዋ ላለው የዘማች ቤተሰብ ጓሮ በማረስ ቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግሯል።

የወጣቶች ማህበር ሰብሳቢ አቶ ደሱ ክፍሌ እንደተናገረው ዛሬ በመገናሴ ቀበሌ ውረር መንደር ተገኝተን ወንድማችን ሀገር ከጠላት ለመታደግ መከላከያ ሄዴ ህይወቱ ስለሰዋ የሚያስፈልጋቸው የተለያዩ ስራ ለመስራት የመገናሴ የከተማና የቀበሌ ወጣቶች አንድ ላይ ተገናኝተን ጓሮ አርሰናል ብሏል።

በቀጣይ ባረስነው እርሻ ላይ ምን እንዝራበት ወይም እንትከልበት ብለን ተወያይተን የምንስራ ሲሆን በመጨረሻም ወጣቶች አሉባልታ ቦታዎች ላይ ከመዋል በየአካባቢያቸው የበጎ አድራጎት ስራዎች እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል ።

በመጨረሻም የዘማች ቤተሰቦቹ የወረዳው መንግስትና ወጣቶች ላደረጉላቸው የመሬት፣የገንዘብና የጉልበት ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋናቸው አቅርቧል ሲል የዘገበው የቸሀ ወረዳ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉ/ፅ/ቤት ነዉ።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

=ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *