ከኢፌድሪ ግብርና ሚኒስትርና ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ የግብርና ኤክስፐርቶች በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ በባድ ቀበሌ በSLM ፕሮጀክትና በማህበረሰብ ተሳትፎ የለሙ የተፋሰስ ልማት ስራዎችን የመስክ ምልከታ አካሄዱ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የግብርና ምክትልና የተፈጥሮ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለምይርጋ ወልደስላሴ እንዳሉት በክልሉ በበጋ የስነ አካላዊና በክረምት የአረንጓዴ አሻራ ስራዎችን ማህበረሰቡ፣ ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞችን በመጠቀም በተሰራው ስራ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ተመዝግበዋል።

በዚህም የከርሰና ገጸ ምድር ውሃ መጨመር ጠቁመው በዚህም የመስኖ ልማት ስራዎችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ አርሶ አደሩ በአመት ሶስት ጊዜ እንዲያመርት ማድረጉን ተናግረዋል።

የመስክ ምልከታው አላማ በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ በአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ የተሰሩ አበረታች ተግባራት በማጠናከር ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማስፋትና ያሉ ጉድለቶች በማረም በዘርፉ በትኩረት ለመስራት ያለመ ነው ብለዋል።

የጉመር ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደገሙ አለሙ በበኩላቸው በወረዳው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በፕሮጀክትና ህብረተሰቡን በማሳተፍ በተሰራው ስራ በዘርፉ አመርቂ ውጤት በመመዝገቡ ከተለያዩ አካባቢዎች በመምጣት ለተሞክሮ ልምድ ጭምር እየተወሰዲ ይገኛሉ ብለዋል።

በዘርፉ የሰብልና የእንሰሳት ምርትና ምርታማነትን እንዲጨምር ከማድረጉም ባለፈ ጠረጴዛማ እርከንና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ከዚህ ቀደም ለእርሻ የማይውሉ የነበሩ በርካታ መሬቶችን ወደ እርሻ በመቀየር ወጣቶች፣ ሴቶች ተደራጅተው በማልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በመስክ ምልከታውም ከአማራ፣ ከትግራይ ከሲዳማና ከሌሎችም ክልሎች የተወጣጡ የግብርርና ኤክስፐርቶች፣ የዞን፣ የወረዳ የስራ ኃላፊዎችና ሌሎችም ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *