ከትምህርት ገበታቸዉ ርቀዉ የነበሩ ከ38 ሺህ በላይ ተማሪዎች ዳግም ወደ ትምህርት ገበታቸዉ እንዲመለሱ ማድረጉም የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያዉ የ2014 ዓመተ ምህረት የግማሽ አመት የአፈጻጸም ግምገማ ከባለድርሻ አካላት ጋር በወልቂጤ ከተማ ለሁለት ቀናት ሲያደርገው የነበረው ግምገማ ዛሬ ተጠናቀዋል።

በትምህርቱ ዘርፉ የሚፈለገዉን ዉጤት ለማምጣት የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ስራ ወሳኝ ነዉ ።

የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አስከብር ወልዴ እንዳሉት ጥራት ያለዉ ትምህርት ለዜጎች ተደራሽ በማድረግና በዘርፉ የሚፈለገዉን ዉጤት እንዲመጣ አጽዕኖት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነም አስታዉቀዋል።

ከትምህርት ገበታቸዉ ርቀዉ የነበሩ ከ38 ሺህ በላይ ተማሪዎች በዘርፉ የሚለከታቸዉ ባለድርሻ አካላቶች ጋር በተደረገ ቅንጅታዊ ስራ ሙሉ ለሙሉ ዳግም ወደ ትምህርት ገበታቸዉ እንዲመለሱ መደረጉም አስረድተዋል።

በትምህርቱ ዘርፍ የሚስተዋሉ ዉስንነቶችን በተገቢዉ በመቅረፍና የትምህርት ጥራት በማሻሻልና ተማሪዎች በስነ ምግባር ታንጸዉ በዉጤታቸዉ ተጨባጭ ለዉጥ እንዲያመጡ ለማድረግ የመማር ማስተማሩ ስራ ከመቼዉም ጊዜ በላይ ትኩረት ሊሰጠዉ እንደሚገባም አብራርተዋል።

ለቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የግብአት አቅርቦት ችግሮቻቸውን በፍጥነት በጥራት ከመፍታት አንፃር የሚስተዋሉ ዉስንነቶች በተገቢዉ መቅረፍ እንደሚገባም አስረድተዋል።

የማስላት እና የማንበብ ክህሎትን በማዳበር ከዝቅተኛው የክፍል ደረጃ ጀምሮ መሰረት መጣል ላይ በማተኮር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ውስንነት እንዲሁም የተማሪዎች ቅበላ በሚፈለገው ደረጃ አለመሳካቱ እና ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ ህጻነት እና ወጣቶች መኖራቸው፣የመምህራን አቅርቦት እና በት/ቤቶች ብቁ አመራሮችን የመመደብ እና በመማር ማስተማር ላይ የማተኮር ችግር መኖሩን ተመላክቷል።

የሳይንስ ትምህርቶችን በቤተ-ሙከራ አስደግፎ ማስተማር ላይ ትኩረት የመስጠት ችግሮች መኖሩን የተናገሩት አቶ አስከብር ቤተ-ሙከራዎች ያላደራጁ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውና ለዚህም በቂ ግብዐት የሌላቸዉ መሆኑም ጠቁመዋል።

ትምህርት በቴክኖሎጂ አስደግፎ የመስጠት ችግር እጅግ የከፋ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያመለክቱ የፕላዝማ፣ የሬዲዮ እና የኮምፒውተር ላብ በመጠቀም የሚሰጠው ትምህርት ዝቅተኛ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ መድረሱንም ጠቅሰዋል።

ተከታታይነትና ቀጣይነት ያለው የመምህራን ክህሎትና ብቃት እንዲሁም ተነሳሽነት የሚያሳድጉ ዘዴዎች ላይ ትኩረት በመስጠት እንዲሁም የትምህርት ብክነትና ብቃትን የሚጎዱ መጠነ-መቅረትና መድገምን፣ የክፍለ ጊዜ ብክነት ወዘተ ለመቀነስ የመምህራን ሚና የጎላ በመሆኑ አጽዕኖት ሊሰጠው እንደሚገባም አሳስበዋል።

አክለዉም ኃላፊዉ በትምህርቱ ሴክተር በመጀመሪያዉ ግማሽ አመት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና የሚስተዋሉ ዉስንነቶችን በተገቢዉ በመቅረፍ በቀጣይ ውጤታማ ስራ መሰራት እንዳለበትም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በግምገማ መድረኩም የተገኙ አንዳንድ ባለድርሻ አካላቶች በሰጡት አስተያየት በትምህርቱ ዘርፍ የተያዙ ግቦች ለማሳካት ከመቼዉም ጊዜ በላይ ትኩረት ሰጥተዉ እንደሚሰሩም አስታዉቀው በዘርፉ የተስተዋሉ ውስንነቶች በፍጥነት ለማረም ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነዉ።

= አካባቢህን ጠብቅ!
= ወደ ግንባር ዝመት!
= መከላከያን ደግፍ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *