ከተሞች በፕላን እንዲመሩ በማድረግና የፕላን ጥሰትን ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ መሆኑም የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ አስታወቀ።


በመሬት ቅየሳ ፈጣንና ዉጤታማ ስራ ለመስራት ዘመናዊ የቅየሳ መሳሪያዎችን መጠቀም የከተሞች እድገትና ለዉጥ እንዲሻሻል ለአራት ወረዳዎች ባለሙያተኞች ለሁለት ተከታታይ ቀናት የተግባርና የክህሎት ሰልጠና በወልቂጤ ከተማ ተሰጥቷል።

የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ምክትልና የከተሞች ፕላን ኢንስትትዩት ሀላፊ ወይዘሮ ሸሚማት ለሻድ እንዳሉት የከተሞች ፕላንና ኢንስትትዩት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ከሚገኙ 6 ዘርፎች አንዱ ነዉ።

ለከተማ ፕላንና ለመሬት ቅየሳ ባለሙያተኞች የተሰጠዉ ስልጠና ከተሞች በፕላን እንዲመሩ በማድረግና የፕላን ጥሰትን ለመከላከል ፋይዳዉ የጎላ እ እንደሆነም ተናግረዋል።

የከተሞች እድገት ለማፋጠን ከዚህ በፊት በባህላዊ መንገድ በሜትር ፣በወረቀት በስኬል እየተለኩ የሚሰሩ ፕላኖች ወደ መሬት የሚወርዱበት ሁኔታ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ዘመኑን ከፈጠረዉ ቴክኖሎጂ ፣ ከከተሞች እድገት አንጻር አዋጭ ስላልሆነና የመሬት ቁጠባ ለማስተዳደር ዉጤታማ ስለማያደርግ ከዘመኑ ጋር መሸጋገር የግድ የሚል እንደሆነም አመላክተዋል።

ዘመናዊ መሳሪያዎች አስፈላጊ ናቸዉ ያሉት ወይዘሮ ሸሚማት ፕላኑን ከዚህ በፊት በቴሲፔፐር ከሚባለዉ ተሸጋግሮ ዛሬ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተደግፎ በጂአይኤስና በቶታል እስቴሽን ወደ ዘመናዊነት የተቀየረ ስለሆነ እነዚህ ዘመናዊ መሳሪያ መጠቀም የግድ እንደሆነም አብራርተዋል።

በዞኑ 4 ወረዳዎች ማለትም ጉመር፣ እኖር ፣ምሁር አክሊል ፣የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳዎች ከፍተኛ ገንዘብ በማዉጣት የመሬት ቅየሳን ፈጣንና ዉጤታማ አገልግሎት መስጠት የማያስችል ቴክኖሎጂ መሳሪያ መግዛት የቻሉ እንደሆነም አመላክተዉ ለነዚህም ትልቅ ምስጋና አቅርበዋል።

መሳሪያዉ ከተገዛ በኋላ ወደ ጥቅም ካልገባ ምንም ዋጋ የሌለዉ እንደሆነና ቶሎ ወደ ተግባር መግባት እንዲችሉ ዘመናዊ የመሬት ቅየሳ መሳሪያ የገዙ ወረዳዎች ለሁት ባለሙያተኞች በመሬት ቅየሳ ዘርፍ የሚፈለገዉን ዉጤት እንዲመጣ ለከተማ ፕላንና ለመሬት ቅየሳ ባለሙያተኞች መምሪያዉ ስልጠና መስጠቱም ተናግረዋል።

የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ባለሙያ አቶ ደምስ ወርቅነህና አቶ ፍቅሩ ልንጋኒ እንዳሉት ቀደም ሲል ሲጠቀሙት የነበረዉን ሜትርና መሰል ቁሳቁሶች ጊዜ ፣ፍጥነትና ጥራት ያለዉ ስራ እንዳየሰሩ ማነቆ ሆኖባቸዉ እንደነበረም አስታዉሰዋል።

ቶታልስቴሽን ዘመናዊ መሰራያዎች በዞንና በወረዳዎች መገዛት የተጀመረ ሲሆን እነዚህ መሳሪያዎች በመጠቀም የመሬት ቅየሳ በማካሄድ የከተሞች እድገትና ለዉጥ እንዲሻሻል ፋይዳቸዉ የጎላ እንደሆነም አብራርተዋል።

ከወረዳ ባለሙያተኞች ጋር ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠር ከተሞች በፕላን እንዲመሩ በማድረግ ከተሞች እንዲያድጉና እንዲለወጡ የማድረጉም ስራ በትኩረት እንደሚሰራም አብራርተዋል።

ሰልጣኞች ባህላዊ አሰራርን በማስቀረት ዘመናዊ መሳሪያዉ በመጠቀም ከተሞች በተሰራላቸዉ ፕላን መሰረት ወደ መሬት በአግባቡ ወርዶ በቂ የሆነ የመሰረተ ልማት ስራዎች እንዲሰሩ ኢንቨስትመንት ማስፋፋት ያስፈልጋልም ብለዋል።

በስልጠናዉ ያነጋገርናቸዉ አቶ መሀመድ አማን እና ወይዘሪት ፋንታዮ ይልማ በሰጡት አስተያየት ቀደም ሲል በስኪል የሚተገበረዉ የመሬት ቅየሳ ስራ ብዙ ችግሮች የሚታይበት እንደነበረም ጠቅሰዉ ዞኑ ዘመናዊ የመሬት ቅየሳ መሳሪያ
የተሻለ ስራ መስራት እንደሚያስችላቸዉም አብራርተዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *