ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው ውብና ጽዱ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ሁሉም ህብረተሰብ በንቃት እንዲሳተፍ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አሳሰበ።


“ብክለት ይቁም ውበት ይንቃ” በሚል መሪ ቃል የግንቦት ወር የአየር ብክለት ለመከላከል ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በይፋ ተጀምራል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ተገኝተው እንዳሉት ባለፉት ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽዱና ውብ ከተሞች ለኢትዮጵያ ብልጽግና በሚል የተጀመረው ስራ በዛሬው እለት በወልቂጤ ከተማ ተጀምራል።

የጉራጌ ዞኑ መቀመጫ ወልቂጤ ከተማ የበርካታ ከተሞች መተላለፊያ መሆኗን ተከትሎ ቆሻሻ በየአካባቢው የሚታይ በመሆኑ ይህንን ለማጽዳት በየሳምንቱ አመራሩና ህብረተሰቡ በጽዳት ዘመቻው በንቃት መሳተፍ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

የጽዳት ዘመቻ ስራው ሰፊ የህዝብ መሰረት እንዲኖረው ማድረግ ይገባል ያሉት አቶ ላጫ ህብረተሰቡ ቆሻሻ ለብክነት መንስኤ መሆኑን በመገንዘብ አካባቢያቸውን ማጽዳት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ከተሞች ውብና ጽዱ ለነዋሪዎች ምቹ በማድረግ ጤናማ ህብረተሰብ ለመፍጠርና ለሰላምና እድገት ወሳኝ በመሆኑ ቆሻሻን የማስወገድ ስራ ህብረተሰቡ በማሳተፍ በተጠናከረ መልኩ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው ውብና ጽዱ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ሁሉም ህብረተሰብ በንቃት እንዲሳተፍም አስተዳዳሪው አሳስበዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ደን አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብረሃም መጫ በክልሉ ለስድስት ተከታታይ ወራት የሚቆይ ዘመቻ ተከትሎ ሚያዚያ የፕላስቲክ፣ ግንቦት የአየር፣ ሰኔ ውሃ፣ ሀምሌ የአፈር ፣ ነሀሴ የድምጽና መስከረም ግምገማ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው።

ከዚህ ቀደም ሚያዚያ ወር ላይ የፕላስቲክ ብክለት ላይ መሰራቱን ገልጸው የግንቦት ወር የአየር ብክለት ለመከላከል በወልቂጤ ከተማ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለመስጠት ያለመ ነው ብለዋል።

ብክለት ማህበረሰቡ ተላላፊና ተላላፊ ባልሆኑ በሽታ እንዲጠቁ ከማድረጉም ባለፈ የአለም ስጋት የሆነው የአየር ንብረት ለውጥ እንዲከሰት ያደርጋል ብለዋል።
የጉራጌ ዞን ደን አካባቢ ጥበቃ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብድልሀፊዝ ሁሴን በአለም ደረጃ የብክለት መንስኤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ቢሄድም ማህበረሰቡ ላይ ሰፊ የግንዛቤ ክፍተት መኖረን ገልጸዋል።

የማህበረሰቡ የግንዛቤ ችግር ለመቅረፍ ንቅናቄ መደረጉን ገልጸው ንቅናቄው ለስድስት ተከታታይ ወራት የሚቆይና በዛሬው እለት የግንቦት ወር የአየር ብክለት ለመከላከል ንቅናቄ ለማስጀመር ነው ብለዋል።

ማህበረሰቡ አካባቢውን ማጽዳት፣ አካባቢን መጠበቅ ባህል አድርጎ እንዲሰራ ለማስቻል መሆኑን ገልጸው በዞኑ የተጀመረው የጽዳት ዘመቻ አጠናክሮ ከማስቀጠልና ከግንዛቤ ጎን ለጎን አካባቢ ብክለት በሚበክሉ ላይ የቁጥትር ስራ እንደሚሰራም ገልጸዋል።

የወልቂጤ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታው ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ ማድረግ የአካባቢ ጥበቃ፣ ጽዳትና ውበት ስራ መስራት ማህበረሰቡ ራሱን ከበሽታ በመከላከልና አካባቢውን በመጠበቅ ጤናማና አምራች ማህበረሰብ ለመፍጠር ሚናው ከፍተኛ ነው።

በዛሬው እለት ጽዱና ውብ ከተማ ለመፍጠር ማህበረሰቡ ለማንቃት ያለመ መሆኑን ገልጸው ማህበረሰቡ ባለቤት በማድረግ በትኩረት መስራት ይገባል።

ወልቂጤ ከተማ ምቹ ለማድረግ የከተማው አመራር፣ የመንግስት ሰራተኞች ማህበረሰቡ በማሳተፍ በየሳምንቱ የጽዳት ዘመቻ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን ያነሱት ከንቲባው ይህም ዘላቂነት እንዲኖረው የተጀመረው ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል ይኖርበታል ብለዋል።

በንቅናቄ ስራው የተሳተፉ አካላት እንዳሉት ከተማዋ ውብና ጽዱ ለማድረግ ከዚህ በፊት በየሳምንቱ በንቃት እንደሚሳተፉ ገልጸው የተጀመረው ንቅናቄ ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም ህብረተሰብ በንቃት መሳተፍ ይኖርበታል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *