ከሬብ የተፈጥሮ ደንን ይተዋወቁ !!

በምሁር አክሊል ወረዳ በርካታ የተፈጥሮ ሀብቶች ያሉ ሲሆን ከነዚህም ከተፈጥሮ መስህቦች አንዱ የከሬብ ደን ነው።

የተፈጥሮ ሀብቶች የአየር ንብረት ሚዛን ፣ብዝሃ ህይወትና ስነምህዳርን ከመጠበቅ አንፃር ፋይዳቸው የጎላ ነው፡፡

የተፈጥሮ መስህቦች ስንል በተፈጥሮ የተገኙ ሐይቆች፣ ወንዞች፣ ተራሮች፣ የተፈጥሮ ደኖች፣ ፍል ውኃዎች፣ ፏፏቴዎች፣ ዋሻዎች፣ የማህበረሰቡ መኖሪያ ቦታዎችና አጠቃላይ ገፅታዎች ያጠቃልላል።

ከሬብ በብዙ አይነት ሃገር በቀል ዛፎችና ወራጅ ወንዞች የተዋበና የሚማርክ አቀማመጥ ያለው ሰፊ አካባቢ ነው።

የከሬብ ደን በምሁር አክሊል ወረዳ ከሚገኙ ደኖች ከፍተኛ ሽፋን የሚይዝ ሲሆን ጥሩ የአየር ንብረት እንዲኖር ከፈተኛ የሆነ ድርሻ አለው ።

የከሬብ የተፈጥሮ ደን በሀገር በቀል ዛፎች የተሸፈነ ሲሆን በወረዳው ውስጥ ከሚገኙ ጥብቅ ደኖች ለአካባበው ግርማሞገስ እንዲኖረው ከማድረጉም በላይ የተለያዩ የዱር እንሰሳት መኖርያ ስፍራ ነው፡፡

ሌላኛው የከሬብ ወንዝ በወረዳው ከሚገኙ ወንዞች አንዱና ትልቁ ሲሆን አጠቃላይ የወረዳውን ተፋስ ከ64 እስከ 70 ፐርሰንት የሚሸፍን ነው፡፡

መነሻው ከምሁር አክሊል ወረዳ ከደጋው አካባቢ የሆነው የከሬብ ወንዝ ለዋቤ ወንዝ ከሚገብሩት ወንዞች በዋናነት ከሚጠቀሱት አንዱና ዋነኛው ነው።

ህብረተሰቡም ሆነ የሚመለከተው አካል የደኑን ጥቅም በመገንዘብ እንደነዚ ተፈጥሮን በተገቢው ለይቶ በመጠበቅ እና በመንከባከብ ጠብቆ ማቆየት ያስፈልጋል።

መረጃው የምሁር አክሊል ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነዉ።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *