ከመቶ ሀምሳ ሚሊዮን ብር በላይ ውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ ግንባታ የውል ስምምነት ተደረገ ።

ከመቶ ሀምሳ ሚሊዮን ብር በላይ ውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ ግንባታ የውል ስምምነት ተደረገ ።

የጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) 1.216 ኪሎ ሜትር ውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ ግንባታ የውል ስምምነት አደረገ።

በውል ስምምነቱም ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን እና የወልቂጤ ከተማ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የማኔጅመንት አካላት በተገኙበት የውል ስምምንት ተከናውኗል።

በወልቂጤ ከተማ የሚጀመረው ከገብርኤል ቤተክርስቲያን እስከ ሰጎመ ትምህርት ቤት ድረስ ያለውን የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ ሥራ ፕሮጀክት ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) ከድርጅቱ የስራ ሃላፊዎች ጋር በዛሬው እለት የውል ስምምነት ስነ ስርዓት ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) በወልቂጤ ከተማ የሚሰራው ውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ ከገብርኤል ቤተክርስቲያን እስከ ሰጎመ ትምህርት ቤት ድረስ ያለው 1.216 ኪሎ ሜትር እና 20 ሜትር ስፋት ያለው የአስፋልት መንገድ በአጭር ጊዜ ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ የውል ስምምነት መከናወኑ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታው ገልፀዋል ።

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የሚገነባ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት የመንገድ ግንባታ ጠቅላላ ወጪ መቶ ሀምሳ ሚሊዮን አንድ መቶ ሰላሳ ሶስት ሺ ስምንት መቶ ሀምሳ ዘጠኝ ከሰላሳ አራት ሳንቲም ብር (150,133,859.34 ) ውል በመግባተ የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ደረጃ በደረጃ ምላሽ ለመስጠት በትኩረት እንደሚሰራ አቶ እንደለ ስጦታው በውል ስምምነቱ ወቅት ገልፀዋል።

ከዚህ በፊት 2013 ዓመተ ምህረት ከተማ አስተዳደሩ
በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ከገብርኤል እስከ ሰጎመ ትምህርት ቤት ውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ስራ አጠቃላይ ቫት ጨምሮ 54,988,47 ብር ውል ቢገባም በተለያዩ ምክንያቶች ማለትም ለፕሮጀክቱ በወቅቱ ምንም አይነት ክፍያ ባለመክፈሉ ፣የወሰን (Right way off) ችግር ባለመፈታቱ ፣የድንጋይ የገረንጋቲ ኳሪ ሳይት ባለማቅረቡ መቋረጡን ከንቲባ አስታውሰው ።

እነዚህ ችግሮችን በመቅረፍ ከተማ አስተዳደር አዲስ የውል ስምምነት በማድረግ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እየሰራ ሲሆን ለዚህ ልማት መፋጠን የከተማው ነዋሪና ህብረተሰብ የበኩሉን በመወጣት አጋዥ በመሆን የተሻለችና የተመረጠች ከተማን በጋራ መገንባት ይጠበቅብናል ብለዋል።

አቶ እንዳለ አክለውም ከተማ አስተዳደሩ ለስራው እንቅፋት ይሆናሉ ያላቸው ጉዳዮች ለይቶ በማውጣት ያለምንም ችግር ስራው በጥራት እና በፍጥነት እንዲሰራ ከፍተኛ ርብርብ እና ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስለተደረገው መልካም ትብብር በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ)ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ዮናስ አያሌው እንደገለፁት ወልቂጤ ላይ የምንሰራው የአስፋልት የመንገድ ስራ በታቀደለት ጊዜ ለመጨረስ ሙሉ ዝግጅት መደረጉን ገልፀዋል ።

ፈጣን የመረጃ ልውውጥ ፈጥረን ስራዎችን እየገመገምን ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲውል የማስቻል ስራ የሁላችን ሀላፊነት አድርገን ልንሰራ ይገባል ሲሉ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ዮናስ ተናግረዋል ።

በውል ስምምነቱ ላይ የተገኙት የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አብድርብር ሰኢድ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) እንደ ሀገር እየሰራቸው ያሉ ስራዎች የሚያስመሰግን ነው ብለዋል።

እንዲሁም ኮርፖሬሽኑ በከተማች የሚሰራውን የመንገድ ስራ ፕሮጀክት በታቀደለት ጊዜና ወቅት እንዲጠናቀቅ ሁሉም አጋዥ ሆኖ በትኩረት እንደሚሰራም ተናግረዋል።

በመጨረሻም በውል ስምምነት ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን እና የወልቂጤ ከተማ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሀላፊዎች እና የማኔጅመን አካላት የኮርፖሬሽኑን የግንባታ ግብአቶች ማምረቻ ማዕከል ጉብኝትና ኮርፖሬሽኑ እያከናወናቸው ያሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ተመልክተው ለአገሪቱ የልማት ስራ ላይ ኮርፖሬሽኑ እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ አድንቀዋል ።

መረጃው የወልቂጤ ከተማ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *