ኧዞኒ የኪነ ጥበብ ቡድን “ጉራጌ” የተሰኘ ትውፊታዊ ቲያትር የተለያዩ ኪነጥበባዊ ስራዎችን በወልቂጤ ከተማ ስራኖ ኢንተርናሽናል ሆቴል አቀረበ።

ኧዞኒ የኪነ ጥበብ ቡድን የጉራጌን ትውፊት እንዲጎለብት ብሎም እንዲተዋወቅ እየሰራ ያለው ስራ በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ።

የኧዞኒ የኪነጥበብ ቡድን መስራችና ስራ አስኪያጅ ሳሙኤል ከበደ እንዳሉት የኧዞኒ ጉራጌ ትውፊታዊ ቲያትር አላማ የጉራጌ ባህል፣ ቋንቋና ሌሎችም እሴቶችን እንዲጎለብቱ ከማድረጉም ባለፈ ለሌሎች ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑንም አንስተዋል።

ጉራጌ የበርካታ ትውፊት ባለቤት ቢሆንም አንዳንዶቹ በመጥፋት ላይ እንዳሉ አንስተው አሁን ላይ የዞኑ ባህል ቱሪዝም መምሪያ እነዚህን ለመታደግንና ለማስተዋወቅ እየሰራ ያለው ስራ የሚበረታታ እንደሆነ አንስተዋል።

ኪነ ጥበብ የአንድን ብሔረሰብ ባህል፣ ቋንቋና ሌሎችም እሴቶችን ከመጥፋት በመታደግ እንዲተዋወቁ ሚናው ከፍተኛ በመሆኑ በዘርፉ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል ብለዋል።

በተለይም ወጣቱ የራሱን ትውፊት ከማወቅና ከመረዳት ይልቅ የሌላውን የመከተል ነገር እንዳለ አንስተው በዚህም ወጣቶች የራሱን ባህል፣ ቋንቋ፣ ታሪክ በተገቢው መረዳት እንዳለባቸው መክረዋል።

ጉራጌያዊ የተሰኘ ትውፊታዊ ቲያትር ላይ የጉራጌ የእርሻ ስርአት የጌዝ፣ የእቁብና የእድር፣ አጀማመር፣ ንግድና ሌሎችም የመድረክ ስራዎች ያቀረቡ ሲሆን ይህም የጉራጌ ቋንቋ ለመታደግና ባህሉን ከፍ ለማድረግ መሆኑን አመላክተዋል።

የጉራጌ ባህል፣ ቋንቋ፣ ታሪክ ከመጥፋት በመታደግ እንዲጎለብትና እንዲተዋወቁ የዞኑ መንግስት እየሰራ ያለው ስራ በቀጣይም ባለሀብቶች፣ መንግስት፣ ወጣቶችና የኪነ ጥበብ ዘርፉ በጋራ በመቀናጀት በትኩረት መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በመድረኩ የተገኙት ታዋቂና ዝነኛ አርቲስት ደሳለኝ አሳምነው ኧዞኒ የኪነ ጥበብ ቡድን የጉራጌ ትውፊት ለማጎልበት፣ ቋንቋው እንዲያንሰራራ በኪነጥበብ ዘርፉ እየተሰራ ያለው ስራ አድንቀዋል።

ወጣቱ ባህሉና እሴቱን ከመከተልና ከመጠቀም ይልቅ የሌላውን የመከተል ነገር እንዳለ ጠቁመው ባህሉን፣ ቋንቋና ሌሎችም እሴቱን ለይቶ እንዲያውቁ ቤተሰብ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

አዞኒ የኪነ ጥበብ ቡድን የጉራጌን ትውፊት ለማስተዋወቅ የጀማመራቸው ስራዎች ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም እገዛ ሊያደርግላቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች እንዳሉት በመድረኩ የቀረቡ የጉራጌ ትውፊታዊ ቲያትር እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።

መድረኩ ከመዝናናት ባለፈ ባህልና ቋንቋቸው ላይ ለመስራት እንዳነሳሳቸውም ገልጸዋል።
የኪነት ቡድኑ የጉራጌ ትውፊት ለማስተዋወቅ ብሎም ቋንቋው እንዲጎለብት እየሰራ ያለው ስራ ይበልጥ በቀጣይም አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያሉት።

ፕሮግራሙ እንዲሳካ ላደረጉ አካላት የምስጋናና የእውቅናና ሽልማት ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *