እየተባባሰ የመጣውን የአየር ንብርት ለውጥ እና አከባቢን የሚበክሉ ቆሻሻዎችን ለማስቅረት በትኩረት መሰራት እንዳለበት ተገለጸ ።

የጉራጌ ዞን ደንና እና አከባቢ ጥበቃ ጽህፈት ቤት አለም አቀፍ የአከባቢ ጥበቃ ቀን በአለም አቀፍ ለ50 ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ30ኛ ጊዜ” መፍትሔ ለፕላስቲክ ብክለት” በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን በሶዶ ወረዳ ዱግዳ ጎሮ ቀበሌ ተከበር።

የ2015 የክርምት ወራት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር የተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት በዛሬው እለት ተጀመረ።

የደቡብ ክልል የደን ልማትና አከባቢ ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ዳምጠው እንደተናገሩት ከአየር መዛባት ጋር ተያይዞ በሀገራችንም በክልላችንም በየጊዜው እየተከሰተ ያለው ድርቅና የጎርፍ መጥለቅለቅ እየተስተዋለ በመሆኑ ይህን በዘላቂነት ለመቅረፍ በርካታ ሰራዎች ተሰርተዋል ።

አንዲሁም ከአካባቢ ብከለት ጋር ተያይዞ ያልተቀረፉ በርካታ ችግሮች መኖራቸውንና ከነዚህም መካከል የብላስቲክ ቆሻሻ በገጠርና በከተማ አከባቢን ከመበከል አልፎ በምርትና ምርታማነት ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ይገኛል ብለዋል ።

እንደ አቶ ዳንኤል ዳምጠው ገለጻ በዘንድሮው ዓመት ብከለት የሚያስከትሉ የደርቅና ፈሳሽ ቆሻሻዎች እና ቆሻሻ ፕላስቲኮችን በማስወገድ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚችሉ አርንጓዴ ኢኮኖሚን መገንባት እንደሆነ ገልጸዋል ።

ዘንድሮ ችግኝ ተከላ የሚካሄድባቸው ለመሬት መንሸራተት የተጋለጡ ቦታዎች ፣ የተጎዱ ተራራማ ቦታዎች መሆናቸውን የተናገሩት አቶ ዳንኤል ዳምጠው በተጨማሪም በከተማ መውጫና መግቢያ በግራና በቀኝ በ 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንደሚተከል ተናግዋል።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን እንደገለጹት የተፈጥሮ ሀብት ውድመት መከላከል አለመቻል የሰው ልጆች አኗኗር ዘይቤን ምስቅልቅሉን እያወጣ ይገኛል ብለዋል።

የደን ውድመት እያስከተለ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ በግብርና ስራ ልማድ መቀየር ፣የዝናብ ወቅቶች መቀያየር ፣የሙቀት መጠን መጨመርና ሌሎችም በርካታ ተግዳሮቶችን እየፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል ።

ምድር ለሁላችንም እኩል እና በዘላቂነት መስጠት የምትችለው የተፈጥሮ ሀብት ያላት መሆኗን የገለጹት አቶ ሙስጠፋ የደርቅና የፈሳሸ ቆሻሻ ፣የተፈጥሮ ሀብት ውድመትን ለማስቀረት በጋራ መራባረብ ይገባል ብለዋል።
የጉራጌ ዞን ደንና እና አከባቢ ጥበቃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት ወንበረጋ እንደገለጹት የአየር ንብርት ለውጥ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሰዎችና እንስሳቶች ከፈተኛ ጉዳት እያደረሰባቸው ይገኛል ብለዋል ።

በመሆኑም ለችግሩ አፋጣኝ መፍትሔ ለማፈላለግ የምንገኝበት ወቅት በመሆኑ የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን በተቀናጀና በተደራጃ መንገድ አመራሩና ማህበረሰቡ በትኩረት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል ።

አሁን የሰው ልጅ በንጹሕ ቦታ የመኖር መብቱን እየተገዳደር ያለው የአከባቢ ብክለት በመሆኑ የገለጹት ኃላፊው ይህን በዘላቂነት ለመቅረፍ በከጠርና በከተማ የቆሻሻ አወጋገድ ስራአት መዘርጋት ይገባል ብለዋል ።

በፕላስቲክ ብክለት ወንዞች ተከበዋል፣መሬት የማልማት አቅማቸው ቀንሰዋል፣በአየርና በአካባቢ ብከለት የተነሳ የብዝሀ ህይወት የመጥፋት አደጋ የተጋርጠባቸዉ እንደሆነና ይህን ለመቀነስ በዚህ የተደራጁ ማህበራትን ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ ብከለትን መቀነስ ይገባል ብለዋል አቶ ምህረት።

አዱኛና ደጉ የደረቅ ቆሻሻ ማጓጓዝና መልሶ መጠቀም ሺርክና ማህበር ተወካይ አዱኛ ጉታ እንደተናገረው ከተማን እየበከሉ ያሉ ኘላስቲክ ቆሻሻዎች በመሰብሰብና በመፍጨት ለሌሎች ፍብሪካዎ በጥሬ እቃነት እያስረከቡ እንደሚገኝ ተናግሯል።
ይህንም ለመስራት ከመንግስት የተለያዩ ድጋፎች እንደቸደረገለትና ተጠናቅሮ እንዲቀጥል ጠይቋል።

አለም አቀፍ የአከባቢ ጥበቃ ቀን በአለም አቀፍ ለ50 ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ30ኛ ጊዜ” መፍትሔ ለፕላስቲክ ብክለት” በሚል መሪ ቃል ችግግኝ በመትከልና የፓናል ውይይት በማድረግ ተከብሯል።

በበአሉም የክልል፣ የዞን፣የከተማና የወርዳ ፣የደንና የአከባቢ ጥበቃ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *