እንኳን ደስ አላችሁ!!!

የወልቂጤ ኤፍ ኤም ሬዲዮ የጉራጊኛ ቋንቋ ስርጭት ዛሬ ምሽት2:00 ሰዓት ጀምሯል።

በኤፍ ኤም 89.2 እና 94.7 ሞገድ ላይ በአማርኛ፣በቀቤንኛ፣ በማረቆኛና በየምኛ ሲተላለፍ የቆየው ስርጭቱ በማስፋት በጉራጊኛ ቋንቋ ስርጭቱን ዛሬ ምሽት 2:00 መጀመሩ ከወልቂጤ ኤፍኤም ሬድዮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የጉራጊኛ ቋንቋ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሬድዮ ስርጭት መዋሉ ማህበረሰቡ ወቅታዊና ትኩስ የሆኑ ዞናዊና ሀገራዊ መረጃዎች በቋንቋው ባለበት ስፍራ ከማግኘቱ ባለፈ ለቋንቋው ልማት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው።

በመሆኑም ለመላው የዞናችን ህዝብ በድጋሚ እንኳን ደስ አላቹ ማለት እንወዳለን።

የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *