ኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዉን ውጤታማ ለማድረግና ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ግንዛቤ የማስጨበጭ ስራዉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ።

መስከረም 11/2015

ኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዉን ውጤታማ ለማድረግና ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ግንዛቤ የማስጨበጭ ስራዉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያው በዘርፈ ብዙ ኤች አይቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ የ2014 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸምና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሄዷል።

የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ተወካይ አቶ አብድልአዚዝ ሹሜ በመድረኩ እንደገለጹት ሴተኛ አዳሪዎች፣የሕግ ታራሚዎች፣የተለያዩ አደንዛዥ እፅ ተጠቃሚዎች፣ወጣቶችና ሌሎች ለበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችና እንዲሁም ለበሽታዉ መዛመት ምክንያት ይሆናሉ በተባሉ በተመረጡ አካባቢዎችን ትኩረት በማድረግ የምርመራና ሻይረሱ የተገኘባቸው ወገኖች ጥራት ያለዉ የህክምና የእንክብካቤ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ የማድረግ ስራ ይሰራል ብለዋል።

በህብረተሰቡ ዘንድ የባህሪ ለውጥ ለማምጣት የወጣቶች አቻ ለአቻ የህይወት ክህሎት ትምህርቶችን ማስተማር እንዲሁም በትምህርት ቤቶች በስፋት ሊሠራ ይገባል ብለዋል።

በየደረጃው በሚፈጠሩ ህዝባዊ መድረኮች፣ በሰነ ጥበብ በማዋዛትናየተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም ስለበሽታው በማስተማር የሻይረሡን ስርጭት ለመቀነስ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

ባለፈው አፈፃፀም ወቅት በጉድለት ከታዩ ተግባራት መካከል ተጋላጭ እና ትኩረት የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ያደረገ ኤች አይቪ ኤድስን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ በቀጣይ ትኩረት ይደረግባቸዋል ተብለዋል ።

በጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ የዘርፈ ብዙ ኤች አይቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ባድበዣ አስፋዉ እንዳሉት ባለፈዉ በጀት አመት የአለም የኤድስ ቀን በማስመልከት በተለያዩ ተጋላጭ ይሆናሉ የተባሉ አካባቢዎች የምርመራ አገልግሎት ለ 658 ሰዎች የተሰጠ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በ 2 ሴቶች ላይ ቫይረሱ መገኘቱም አስታዉሰዋል።

በዞኑ 4481 ሻይረሱ በደማቸው የተገኘባቸው ወገኖች መኖራቸዉም አስረድተዉ ኤች አይቪ ኤድስ አሁንም ማህበረሰቡን እየተፈታተነ መቀጠሉም ጡቁመዉ ማህበረሰቡ ሳይዘናጋ በዘርፉ የተጣሉ ግቦችን በተሻለ መልኩ በመፈፀም የቫይረሱ ስርጭት ለመቆጣጠር በጋራ መረባረብ ይገባል ብለዋል።

በቀጣይ ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ወገኖችን ለመንከባከብና ለመደገፍ የባለሀብትና የመላው ማህብረተሰብ ተሳትፎን በተሻለ መልኩ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

አንዳን የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት መድረኩ ለቀጣይ ስራ የበለጠ የሚያነሳሳ እነደነበረ ተናግረዋል ።
ዘርፉን በግብዓትና በፋይናንስ የሚረዱየአጋር ድርጅቶች ቀጥር አየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ የሚፈጠሩ ክፍተቶች ለመቀነስ ከወዱሁ አንደሚሰሩ ተናግሯል ።
ከዞኑ አቅም በላይ የሆኑ በሽታውን ለመመርመና ተጓዳኝ የአባለዘር በሽታዎችን ለማከም የሚረዱ የተለያዩህክምና ግብዓቶቾ የሚመለከተው ችግሩን ሊቀርፍ እንደሚገባ አሰተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል ።
ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *