አድማስ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ካፒታሉን ከማሳደግ ባሻገር የኑሮን ውድነት ለማረጋጋት እየሰራ ያለውን ተሞክሮ ቀምሮ ለማስፋት እንደሚሰሩ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የድሬዳዋ ከተማና ህብረት ስራ ኤጀንሲ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በጉራጌ ዞን ከአድማስ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን የልምድ ልውውጥ አደረጉ፡፡

በልምድ ልውውጡ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማልና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርን ጨምሮ የከተማዉ አስተዳደሩ የህብረት ስራ አመራሮች ተገኝተዋል።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር አድማስ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን በአነስተኛ መነሻ ካፒታል ስራ ጀምሮ በአሁን ወቅት ከፍተኛ እድገት እያስመዘገበ የሚገኝ ተቋም እንደሆነ ባደረጉት የልምድ ልውውጥ ማረጋገጥ እንደቻሉ ገልፀዋል፡፡

ዩኒየኑ ውስጥ ካፒታሉን ከማሳደግ ባሻገር ህብረተሰቡን እየተፈታተነ የሚገኘው የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት እየሰራ ያለውን ስራ ተሞክሮ ቀምሮ በማስፋት የከተማው ህብረተሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰሩ አስረድተዋል፡፡

እንደ ከንቲባው ገለፃ ዩኒየኑ ለሚያመርተው ዘይት የኑግ ምርት ሙሉ በሙሉ ከአርሶ አደሩ መቅረቡ አርሶ አደሮችን ይበልጥ ተጠቃሚ እያደረጋቸው እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ለዩኒየኑ ውጤታማነት በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ዩኒየኑ ተሞክሮ ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ጀማል በበኩላቸው አድማስ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን አስፈለጋውን ድጋፍ ይደረግለታል ብለዋል፡፡

ዩኒየኑ ከዘይት ምርት በተጨማሪ የጉራጌ ቡና በዓለም ደረጃ ለማስተዋወቅና በዘርፉ የተሰማሩ አካላት ተጠቃሚ ለማድረግ የጀንፈል ቡና ማበጠሪያ ፋብሪካ ግንባታ ስራ ተጠናቆ ወደ ተግባር መግባቱን አቶ መሀመድ ገልፀዋል፡፡

የድሬዳዋ ህብረት ስራ ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ መሀመድ አሜ በሰጡት አስተያየት በኑግ ምርት የተሰማሩ አርሶ አደሮች የገበያ እድል እንዲያገኙ ከማስቻል ባለፈ ዩኒየኑ በአርሶ አደሮች ተቋቁሞ ወደ ፋብሪካ ደረጃ ማደግ መቻሉ የሚበረታታ ነው፡፡

በመሆኑም ዩኑየኑ አሁን ለደረሰበት ደረጃ የተኬደበት መንገድ ተሞክሮ ተቀምሮ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰሩም አስረድተዋል።

የአድማስ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ስራ አስኪያጅ አቶ አበበ ወርቅነህ የዩኒየኑ ልምድ ባካፈሉበት ወቅት የዩኒየኑ አባላት ያላቸው የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅም በማስተባበር ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ መሸጋገር የሚችሉባቸው ተግባራት ለማየት እድል ፈጥሮላቸዋል፡፡

በልምድ ልውውጥ ወቅት የተሰጡ አስተያየቶች ለዩኒየኑ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥሩ በመሆናቸው ከዞኑ አስተዳደር ጋር በመተባበር ተግባራዊ እንደሚያደርግላቸው ገልጸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው፡፡

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *