አበኬ ደን በጉመር ወረዳ ከሚገኙ የቱሪስት መስህብ/መዳረሻ አንዱ ነው፡፡

ነሀሴ 20/2014

አበኬ ደን

አበኬ ደን በጉመር ወረዳ ከሚገኙ የቱሪስት መስህብ/መዳረሻ አንዱ ነው፡፡ ደኑ 76.96 ሄክታር የሚሸፍን ሲሆን የወረዳው ዋና ከተማ ከሆነችው አረቅጥ በ5.5 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከዞኑ ዋና ከተማ ወልቂጤ በ73.5 ኪ.ሜ፣ ከመዲናችን አዲስ አበባ ደግሞ 224.5 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡

ደኑ ከሌሎች የተፈጥሮ ደኖች ለየት የሚያደርገው ሰው ሰራሽ መሆኑ ሲሆን በውስጡ የተለያዩ የቱሪዝም ሀብቶች ይዟል፡፡ በደኑ ውስጥ ከሚገኙ የቱሪዝም ሀብቶች ውስጥ ለአብነትም ያህል ስንጠቅስ የዱር እንስሳት ከርከሮ፣ ጅብ፣ ሚዳቆ እና አሳማ ይገኛሉ፡፡

የእፅዋት ዝርያ ኮሶ፣ ግራቪሊያ፣ ወይራ፣ ባህር ዛፍ፣ የሃበሻ እና የፈረንጅ ፅድ ይገኛል፡፡ የተለያዩም የአዕዋፍት ዝርያዎች ይገኛሉ በደኑ ውስጥ፡፡

አበኬ ደን የ37 አመት እድሜ ያስቆጠረ ሲሆን ሰው ሰራሽ እንደመሆኑ መጠን የመጀመሪያ ተከላ የተደረገው በ1977 ዓ.ም በደርግ ዘመነ መንግስት እንደነበርና በ2009 የማስፋፊያ ተከላ መደረጉ ከጉመር ወረዳ አካባቢ ደን ጥበቃ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል ሲል የዘገበው የጉመር ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዱዮች ጽ/ቤት።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *