አሸባሪው የህዋሀት ቡድን በሴቶችና ህጻናት እንዲሁም በሰላማዊ ህዝብ ላይ እያደረገ ያለው የጅምላ ጭፍጨፋንና ጥቃት የሚቃወም ዞናዊ የሴቶች ሰልፍ በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ ተካሄደ፡፡

የዞኑ ሴቶች ከመንግስትና ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመሆን ከሚያደረጉትን ቁሳዊ ድጋፍ ባለፈ አስከ ግንባር ለመዝመት ቁርጠኛ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡

የደቡብ ክልል ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ኩሪባቸዉ ታንቱ በሰልፉ ላይ እንደገለጹት የህወሃት ቡድን በሀገሪቷ ላይ ዘርፈ ብዙ ጭካኔ የተሞላበት ወንጀሎችን መፈጸሙንና ሴቶች ይህንን ቡድን ለማጥፋት ለሚፋለመው ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደጀን በመሆን፣ስንቅ በማዘጋጀት፣ልጆቻቸውን መርቀው በማዝመት እንዲሁም የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ንቁ ተሳትፎ አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ መሰረት አመርጋ እንደገለጹት የጉራጌ ዞን ሴቶች ተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉበት ዋነኛ አላማ የምእራባዊያን ጣልቃ ፈጽሞ አያስፈልግም ኢትዮጵያ ሉአላዊ ሀገርና የጥቁር ህዝቦች ኩራትና የነጻነት ተምሳሌት መሆኑዋን ተናግረዋል፡፡

አሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ በሴቶችና ህጻናት እንዲሁም በሰላማዊ ህዝብ ላይ እየፈጸሙት ያለውን ጥቃት ለመቃወም ያለመ ሰልፍ መካሄዱን ወ/ሮ መሰረት ተናግረዋል፡፡

አክለዉም የዞኑ ሴቶች ትናትም ዛሬም እያደረጉት ያለው ድጋፍ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን የተናገሩት ኃላፊዋ እንደ ዞን ለ5ኛ ዙር ለመከላከያና ለተፈናቃይ ወገኖች ከ1 መቶ 45 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ መደረጉንና ከዚህም ውስጥ 45 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆነው ሴቶች የተሳተፉበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ገብረ መስቀል በበኩላቸዉ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ሀገርን ለማዳን ጦሩን ለመምራት ከዘመቱ በኃላ ለወሬ ነጋሪ እስኪጠፋ ድረስ አሸባሪ ቡድን ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሰራ ደርሶበታል ብለዋል፡፡

አክለውም ከቀናት ቡኃላ አዲስ አበባ እገባለሁ ያለው ቡድን በመከላከያ ብርቱ ክንድ እየተደመሰስና እየተማረከ በሞት አፋፍ ላይ ሁኖ በተለያዩ የውጭ ሚዲያ ዎች በመታገዝ የሀሰት ፕሮፓጋንዳው እያሰራጭ ህዝቡን ቢያደናግርም በቅርብ ቀን ግበአተመሬቱ እንደሚፈጸም ከንቲባዉ ተናግረዋል፡፡

አንዳንድ ያነጋገርናቸው ሰልፈኛ ሴቶች በሰጡት አስተያየት ጁንታዉ በሴቶችና ህጻናት ላይ እያደረሰ ያለው ጥቃት እንዲሁም በህዝቦች ላይ እያደረገ ያለው ጅምላ ጭፍጨፋ እንደሚያወግዙ ተናግረዋል፡፡

አስተያየት ሰጪዎቹ አክለዉም ከመንግስትና ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመሆን ከሚያደረጉትን ቁሳዊ ድጋፍ ባለፈ አስከ ግንባር ለመዝመት ቁርጠኛ መሆናቸዉን ገልጸዋል፡

፡በሰልፉ ላይ የክልል አመራሮች፣የዞን ፣የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር፣ የቀቤናና የአበሽጌ ወረዳ አመራሮችና ሴቶች እንዲሁም ነዋሪዎች ተሳትፈዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮምንኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው፡፡

= አካባቢህን ጠብቅ!
= ወደ ግንባር ዝመት!
= መከላከያን ደግፍ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGv

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *