አስተማሪያቸው (የቀለም አባታቸው) የደበደቡ ተማሪዎች በ2 ዓመት ከ3 ወር እስራት ተቀጡ።

አስተማሪያቸው (የቀለም አባታቸው) በመደብደብ የመንግስት ስራ እንዲስተጓጎል ያደረጉ ተማሪዎች በ2 ዓመት ከ3 ወር እስራት ተቀጡ።

በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በኩር ክፍለ ከተማ አዲስ ሕይወት ቀበሌ ውስጥ በሚገኘው ህዳሴ ፍሬ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የሆኑት ሁለት ተከሳሾች የትምህርት ቤቱ ዋና ርዕሰ መምህር ቢሮ ድረስ በመግባት በመደብደብ ጉዳት ያደረሱበትና መደበኛ የመንግስት ሥራውን በአግባቡ እንዳይሰራ ያስተጓጎሉ በመሆኑ በአንድ ድርጊት ሁለት የወንጀል ድንጋጌዎችን በመተላለፍ የወልቂጤ ከተማ ዐቃቤ ሕግ በሁለት ክስ መስርቶ በፍርድ ቤት አቅርቧቿዋል።

ይህ የዐቃቤ ሕግ ክስ ከመጥሪያ ጋር ለተከሳሾች ደርሷቸው ችሎት ከቀረቡ በኋላ የወንጀል ድርጊቱን ለመፈፀማቸው ሲጠየቁ ተማሪዎቹ አስተማሪያቸውን በዲሲፕሊን ምክንያት የ10ኛ ክፍል ፈተና እንዳይፈቱኑና እንዳይማሩ በመታገዳቸው ቅሬታ አቅርበው እያለ ምላሽ ሰላልተሰጠን በሚል ርዕሰ መምህሩ ቢሮ ውስጥ ስራውን እየሰራ ባለበት ገብተው ድብደባ መፈፀማቸው አምነዋል።

ዐቃቤ ሕግም ተከሳሾቹ የወንጀል ድርጊቱን ለመፈፀማቸው በዝርዝር ያመኑ ስለሆነ ባመኑት መሰረት የጥፋተኝነት ውሳኔ ይሰጥልኝ በማለት ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱም ሌላ ማስረጃ መስማት ሳያስፈልግው ባመኑት መሰረት ተከሰው በቀረቡበት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 438 እና 556/1/ ስር የጥፋተኝነት ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ለወደፊቱ ትምህርት እንዲሆናቸውና ሌሎችም መሰል ጓደኞቻቸው እንዲማሩበት በማሰብ እያንዳንዳቸው በ2 ዓመት ከ3 ወር እስራት እንዲቀጡ በማለት የወልቂጤ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሐምሌ 5 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት ላይ ውሳኔ ሰጥቷል።

ውሳኔውም ተከሳሾቹ ለወደፊቱ የእስራት ጊዜአቸውን ጨርሰው ሲወጡ ታርመውና ታንፀው ጥሩ ዜጋ ይሆናሉ።

ሌሎችም ዓመቱን ሙሉ ትምህርታቸውን ባግባቡ ሳይከታተሉ ይቆዩና በዓመቱ መጨረሻ ያልሰሩትን የፈተና ውጤት ይሰጠን የሚሉ ተማሪዎችና የቀለም አባታቸውን/አስተማሪያቸውን/ ከመደብደብ ፣የትምህርት ቤታቸውን ንብረት ከማውደም ይቆጠባሉ ይማራሉ የሚል አስተማሪ ውሳኔ መሆኑ ተገልጿል።

ወላጆችም ልጆቻቸው ትምህርታቸው በአግባቡ ለመከታተላቸው ተገቢውን ክትትል እንዲያደርጉና ከትምህርት ቤት ውጪም የት እንደሚውሉ መቆጣጠር አለባቸው በማለት የወልቂጤ ከተማ የመጀመሪያ ጀረጃ ፍርድ ቤት መልዕክት አስተላልፏል ። ዘገባው የወ/ከተ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።

ሊንኮቻችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *