አሰራራቸውን በማጠናከርና በማሻሻል በዘርፉ የሚፈለገዉ ውጤት እንዲመጣ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው የጉራጌ ዞን ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ።

የጉራጌ ዞን ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት እና ዩኒየኖች በወቅታዊ የኑሮ ውድነትና ተገቢነት በሌለዉ የዋጋ ጭማሪ ዙሪያ የምክክር እና የተግባር አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሄደዋል።

በምክክር መድረኩ የተገኙት የጉራጌ ዞን ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን ነጋሽ እንዳሉት የህብረት ስራ ዩኒየኖች አሰራርና አደረጃጀት በማጠናከር በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በማረም ለማህበረሰቡ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በማድረግ ሀገራዊ ሁኔታን ያገናዘበ ስራ መስራት ይኖርባቸዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተስተዋለ ያለውን የፍጆታ እቃዎች የዋጋ ጭማሪ ተከትሎ በዞኑ የሚስተዋለዉን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም ህብረት ስራ ዩኒየኖች ያሉትን ማነቆዎች በጋራ በመፍታት አመርቂ ስራ መሰራት እንዳለባቸዉ አስገንዝበዋል ።

በዞኑ የሚገኙ ህብረት ስራ ማህበራት በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚዉ እድገት ላይ አሰተዋጾኦ እያደረጉ እንደሆኑም አስረድተዉ ተገቢ ያልሆነ የገበያ ንረት እና የኑሮ ዉድነት እለት ከእለት እያደገ በመምጣቱ ለማርገብ በትኩረት መስራት እንዳለባቸውም ገልጸዋል ።

አክለውም በዞኑ የሚኖሩ የህበረተሰብ ክፍሎች ሀብትን መስረት በማድረግ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ችግሩን ለመፈታት የህብረት ስራ ማህበራትን በማጠናክር አቅማቸዉን በመገንባት፣ የግብይት ድርሻዉን በማሳደግ፣የቁጠባ ባህላቸዉን በማጠንከርና በማሳድግ የማበድርና የመበደር አቅም በመፍጠር፣ ፣ህጋዊነታቸዉን እና ደህንነታቸዉን በማስጠበቅ የአባላትን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

ህብረት ስራ ዩኒየኖች አነስተኛ ገቢ ላላቸዉ የከተማ ነዋሪዎች አስፈላጊ የሆኑ የፍጆታ እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርቡ በማድረግ በዞናችን አሁን የሚታዩ የዋጋ ንረት ለማረጋጋት በኃላፊነትና በትኩረት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል ።

የምክክር መድርኩ ተሳታፊዎች መካከል የዋልታ ዩኒየን ስራ አስኪያጅ አቶ ወልዴ ቱፈር እና የአግኖት ዩኒየን የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተሾመ በሸ እንደገለጹት እስካሁን ብድር የማመቻቸትና በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን ቢያቀርቡም አጥጋቢ እንዳልሆነ ገልጸዋል ።

በቀጣይ ያሉባቸውን ተግዳሮቶች በመፍታትና በማረም በቻሉት መጠን እየተስተዋለ ያለውን የኑሮ ውድነት ለማርገብ በትኩረት እንደሚሰሩም አመላክተዋል ።

በምክክር መድረኩም የጉራጌ ዞን ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን ነጋሽ ጨምሮ ፣ የህብረት ስራ ዩኒየን ስራ አስኪያጆች ፣የቦርድ ሰብሳቢዎች ፣የቁጥጥር ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ፣የልማት ዕቅድ ባለሙያዎች ፣የዞኑ ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት ማኔጅመንትና ከፍተኛ ባለሙያዎች ተገኝተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *