አርሶ አደሮች የኩታ ገጠም አስተራረስ ዘዴ ተጠቅመው በማረሳቸው ምርትና ምርታማነትን በማሳደጉ እረገድ እየመጣ ያለው ለውጥ አመርቂ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።



በጉራጌ ዞን ምስራቅ መስቃን ወረዳ በዶበና ባቲ፣ በዶበና ጎላና በወጃ ባቲ ቀበሌዎች የመኸር እርሻ የልማት እንቅስቃሴ የዞን፣ የመስራቅ መስቃንንና የ አጎራባች ወረዳ አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና አርሶ አደሮች በተገኙበት የመስክ ጉብኝት ተካሄደ።
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል በጉብኝቱ ተገኝተው እንደገለፁት አርሶ አደሩ ከዚህ በፊት የነበረው ነባራዊ ሁኔታ ሳይበግረው የወረዳው አርሶ አደር ሞዴል የሆነ ልማት ሰርቶ ማሳየቱ ሊበረታታ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል ።
ወረዳው በመሰረተ ልማት እያደጉ ካሉ ወረዳዎች አንዱ መሆኑን ያሳወቁት አቶ መሀመድ ጀማል መሟላት ያለባቸው መሰረተ ልማቶች እና የግብርና ግበአቶች በቀጣይ እንዲሟሉ ይደረጋል ብለዋል።
አርሶ አደሮች የኩታ ገጠም አስተራረስ ዘዴ ተጠቅመው በማረሳቸው ምርትና ምርታማነትን በማሳደጉ እረገድ እየመጣ ያለው ለውጥ አመርቂ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አቶ መሀመድ ጀማል አሳስበዋል።
አርሶ አደሩ በቀጣይ ጊዜያትም መሬቱ ጾሙ እንዳይከረም በትጋት በመስራትና የኑሮ ውድነቱ ለመቀነስ በግብርናው ሊተጋ ያስፈልጋል ብለዋል።
አርሶ አደሩ የሚያነሳቸው የግብርና ግብዓቶች፣ ቴክኖሎጂዎች፣ ማሽነሪዎች፣ ኬሚካሎች እና የመሰረተ ልማቶች ዝርጋታዎች ሀገሪቷ አሁን ካለችበት ፈተና በማውጣት በቀጣይ ደረጃ በደረጃ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለመፍታት ጥረት እንደሚደተግ ተናግረዋል።
የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ክፍሌ ለማ በበኩላቸው አርሶ አደሮች የ1ለ5 አደረጃጀቶቻቸው በማጠናከር በግብርናው ያሳዩት መልካም መነሳሳት ወንድማማችነትና አንድነታቸውን አጠናክረው ከግብርናው ስራ ሳይነጠል ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች መሰረት በማድረግ ተጠናክረው መስራት እንደሚኖርባቸው መክረዋል።
አርሶ አደሩ ይቻላል ብሎ በመስራቱና ውጤታማ መሆኑን በተግባር አሳይቷል ያሉት አቶ ክፍሌ አርሶ አደሮን ቴክኖሎጂን የመጠቀ እንዲሁም በመስመር የመዝራት ፍላጎቱን እየጨመረ በመምጣቱ ግብርናውን ማሳደግ እየተቻለ መሆኑን ጠቁመዋል።
የጉራጌ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሸምሱ አማን የተጎበኙ የመኸር ስራዎች 80 ፐርሰንቱ በክላስተር የለሙ ናቸው ብለዋል። እነዚህም ከ15 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ መሆናቸው በማሳወቅ።
በዞኑ የምርጥ ዘር አጠቃቀም ተግባራዊ አድርገው ከሚተገበሩ ወረዳዎች ምስራቅ መስቃን አንዱ በመሆኑ ከዞኑ አልፎ ለክልል የምርጥ ዘር አቅራቢ ወረዳ እንዲሆን የተጀመረው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳውቀዋል።

በዞኑ በመኸር አመቱ አርሶ አደሮች ምርጥ ዘር እንዲጠቀሙ እና በመስመር እንዲዘሩ በመደረጉ አመርቂ ለውጦች እየታየ ይገኛል ነው ያሉት። በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች በማስፋት መላው አርሶ አደር ይበልጥ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ ሁሉም አመራርና ባለሙያ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባልም ብለዋል።
የምስራቅ መስቃን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመዲን ደድገባ በንግግራቸው ወቅት እንደገለፁት የወረዳው አርሶ አደር ሀገር ለማዳን በሚደረገው ዘመቻ ልጁ ሳይቀር ወደ ግንባር መላኩንና በተቻለው አቅም ሁሉ ድጋፍ ማድረጉን አድንቀው ድህነትን ለመዋጋትና ረሃብ እንዳይኖር አርሶ አደሩ የግብርናውን ስራ ዋናው ተግባሩ በመሆኑ ይበልጥ አጠንክረው እንዲሰሩ ጠይቀዋል።
በጁንታ ድብቅ ሴራ የወረዳው ማህበረሰብ ከማረቆ ብሔረሰብ ሲባላና ሲያዋጋ እንደነበር አቶ አህመዲን ደድገባ አስታውሰው በአሁን ሰዓት ህብረተሰቡ ቀድሞ ወደ ነበረበት ሰላሙ ተመልሶ በሰላም እየኖረና ልማቱን እያፋጠነ እንደሚገኝም አሳውቀዋል።
በወረዳው ከሚለሙት ሰብሎች ባቄላ፣በርበሬ፣ማሽላ፣ገብስ እና ጤፍ ተጠቃሽ ሲሆኑ በመኸር እርሻ ወቅት 4137 ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ 4137 ሄክታር መሬት በነዚህ ሰብሎች መሸፈኑን ተናግረዋል።
አቶ ቶፊቅ አድማማ እና አቶ አብዶ ሁሴን
በጉብኝቱ ከተሳተፉ በርካታ የወረዳው አርሶ አደሮች መካከል አቶ ቶፊቅ አድማማ እና አቶ አብዶ ሁሴን ይገኙበታል። እንደርሱ ገለፃ ምርጥ ዘርና ማደበሪያ የግብርና ባለሙያ ባሰለጠናቸው መሰረት በአግባቡ በመጠቀምና ከማሳ ዝግጅት እስከ አረም ቁጥጥር ድረስ በክላስተር ካሉ አርሶ አደሮች በጋራ በመተባበር ሲሰሩ መቆየታቸው ተናግረዋል።
በበልግና በመኸር እርሻ ወቅት በጋራ በሰሩት ስራም ምርትና ምርታማነታቸውን እንደሚጨምርና ከሌላው ገዜ በተሻለ ውጤታ እንደሚሆኑ ገልፀዋል።
አርሶ አደሮቹ አያይዘውም መንግስት ከቅርብ ጊዜ የጀመረው የሜካናይዝድ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የአርሶ አደሩ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን በፍጥነት እንዲያድግ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በተለይም ለመስኖ አገልግሎት የሚያገለግሉ የውሃ ፓንፖች፣ ጀነሬተር እና ኮምባይነር እንዲሁም ሌሎች መውቂያ ማሽኖች መቅረብ እንዳለባቸው ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስትን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *