አርሶ አደሮች አዳዲስና የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ ድጋፍ እንደሚያደርግ የደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ ገለፁ።

በጉራጌ ዞን በሶዶ እና መስቃን ወረዳዎች በመኸር ወቅት የተከናወኑ የኩታ ገጠም ሰብሎች በክልሉ፣ በዞንና በወረዳ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎችና አርሶ አደሮች ተጎበኙ።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው እንደተናገሩት ሀገሪቱ የገጠማት ጦርነት በብቃት በመመከት ሉአላዊነቷን ከማስጠበቅ ጎን ለጎን ዜጎች በግብርናው ዘርፍ በመሰማራት የምግብ እጥረት ለመከላከልና የኢኮኖሚ አሻጥሩ ለመቋቋም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መስራት ይጠበቅባቸዋል።

በጉራጌ ዞን ሶዶ እና መስቃን ወረዳዎች የተጀመረው ኩታ ገጠም የሰብል ልማት ውጤታማ እና በአርአያነት የሚጠቀስ በመሆኑ ምስጋናቸውን ያቀረቡት አቶ እርስቱ ይርዳው አርሶ አደሮቹ በተለይም ወጣቶችና ሴቶች የጀመሩትን ተግባር አጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል።

በመሆኑም አርሶ አደሮች ከማሳ ዝግጅት ጀምሮ ምርት እስኪሰበሰብ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ድጋፍ ይደረግላቸዋል ያሉት ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ የመንግስት አቅም ውስን ቢሆንም አርሶ አደሮች በመደራጀት የሚፈልጉትን ቴክኖሎጂ ከታክስ ነጻ የሚሆኑበት እና በበድር የሚገዙበት እድል እንደተፈጠረላቸው አስረድተዋል።

እንደ አቶ እርስቱ ገለጻ ሶዶ ወረዳ በግብርናው ዘርፍ ላይ ይበልጥ ውጤታማ እና አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ በግብርና እድገት ፕሮግራም (AGP) ተጠቃሚ ይደረጋል ብለዋል።

በመሆኑም የወረዳው አርሶ አደሮች በአመት እስከ ሶስት ጊዜ በማምረት ተጠቃሚ ለማድረግ የመስኖ ፕሮጀክት ስራ በ2014 ዓ.ም እንደሚጀመር አስረድተዋል።

የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ በበኩላቸው በመኸር ወቅት የምርት ድርሻ፣ የተፈላጊነት ደረጃ፣ አካባቢ የማልማት ደረጃ እና ሳይታረስ የሚያድር መሬት እንዳይኖር ተደርጓል።

አካባቢዎቹን በመለየት በተደራጁ ወጣቶችና ሴቶች እንዲለሙ ብለዋል።

ምርታማነትን ለማሳደግ ሰብልን በክላስተር እንዲለማ ማድረግ፣ አርሶ አደሮች ትራክተር በብድር እንዲያገኙ ማድረግና ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎች ትኩረት ከተሰጣቸው ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ እንደሆነ አቶ አንተነህ አስገንዝበዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ጀማል እንደተናገሩት በዞኑ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያግዙ 30ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር፣ ከ3 መቶ ሺህ በላይ ኩንታል ማዳበሪያና ኬሚካሎች ለአርሶአደሮች ማቅረብ ተችሏል።

በተጨማሪም መንግስት በፈጠረው የብድር አገልግሎት 44 ትራክተሮች የተገዙ በመሆኑ በዞኑ በመኸር ወቅት ከለማው ማሳ 80 በመቶ የሚሆነውን ማሳ በኩታ ገጠም ለማልማት አስችሏል ብለዋል ።

በዞኑ በተያዘው የመኸር ወቅት 142 ሺህ 633 ሄክታር መሬት እየለማ መሆኑ የተናገሩት አቶ መሀመድ በሽምብራ እና በጓያ ከሚለሙ ማሳዎች ውጭ ያሉትን ማሳዎች በዘር እንደተሸፈነ ገልጸዋል።

ጉብኝቱ የሶዶ ወረዳ በስንዴ ምርት ያለውን የምርታማነት ተሞክሮ ለማስፋት የሚያስችል ሲሆን አርሶአደሮች ሰብሎቻቸውን ይበልጥ መንከባከብ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

አርሶ አደሮቹ ሰብሎቻቸው በኩታ ገጠም ማልማታቸው ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው አስረድተዋል።

እንደ አርሶአደሮች ገለጻ ኩታ ገጠም አሰራር የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በአንድ ማእከል እንዲያገኙ አስችሏቸዋል።

ይህ ደግሞ በምርትና ምርታማነት እድገት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚኖረው በመሆኑ ተጠቃሚ እንደ ሚያደርጋቸው ገልጸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *