አርሶ አደሮች በተሻሻለ የእንስሳት ዝርያ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ

በዞኑ የ2015 ዓ.ም ዞናዊ የሆርሞን ማድራት ተግባር በተለያዩ ወረዳዎችና ከተሞች ተጠናክሮ መቀጠሉን ተመልክቷል።

በጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ የእንስሳትና አሳ ሀብት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሀመድ ሙደሲር አርሶ አደሮች በተሻሻለ የእንስሳት ዝርያ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ መምሪያው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

የ2015 ዞናዊ የሲንክሮናይዜሽን መርሀግብር በዞኑ በምዕራብ ክላስተር በሚገኙ አምስት ወረዳዎችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች እየተከናወነ ሲሆን እዣ፣ እኖር፣ ጌታ፣ ገ/ጉ/ወለኔ፣ ጉመር ወረዳዎች እንዲሁም አገና እና አረቅጥ ከተማ አስተዳደሮች የተሰለፈበት አፈጻጸም ማስመዝገብ መቻላቸው ኃላፊው ገልጸዋል።

እንደ አቶ መሀመድ ገለጻ በመጀመሪያ ዙር ተለይተው ከቀረቡ አንድ ሺህ 416 የዳልጋ ከብት መካከል አንድ ሺህ 301 የሚሆኑት ለሆርሞን ዝግጁ በመሆናቸው 689 የዳልጋ ከብቶች ሆርሞን የተወጉ ሲሆን 166 የዳልጋ ከብቶች በቀኑ ቀጥታ ማዳቀል ተችሏል።

ዝግጁ ያልሆኑ(CL-ve) 244፣ እርጉዝ የሆኑ (Pd+ve) 108፣ ለሆርሞን መልስ ሠጥተው የተዳቀሉ 265 በሁለቱም የተዳቀሉ 431 ሲሆነ ድቀላው ሆርሞን ከወሰዱበት ለተከታታይ 7ቀን ውስጥ የሚያልቅ ስለሆነ ሆርሞን የወሰዱት ሙሉ ለሙሉ ይዳቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *