አርሶ አደሮች በበልግ እና በመኸር እርሻ ልማት በተለያዩ ሰብሎች የሸፈኗቸው ማሳዎች የሰብል ቁመና አርሶ አደሩ የሚጠበቀው ምርት ሊያስገኝ እንደሚችል ተገለፀ።

ነሀሴ 11/2014 ዓ.ም

አርሶ አደሮች በበልግ እና በመኸር እርሻ ልማት በተለያዩ ሰብሎች የሸፈኗቸው ማሳዎች የሰብል ቁመና አርሶ አደሩ የሚጠበቀው ምርት ሊያስገኝ እንደሚችል ተገለፀ።

የአበሽጌ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች የበልግ ሰብሎችና የመኸር እርሻ ስራ ያሉበት ወቅታዊ ሁኔታ በመስክ ተዛዙረው ተመልክተዋል።

የአበሽጌ ወረዳ ጤፍ፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ቦለቄ እና መሰል የአዝርእት ሰብሎች በከፍተኛ መጠን አብቃይ አካባቢ ከመሆኑም ባሻገር የበርበሬ አምራች አርሶአደሮች ይገኙበታል።

በዘንድሮው የበልግ እና የመህር የእርሻ ልማት ከ34 ሺ 9 መቶ ሄክታር መሬት በላይ ለማልማት የታቀደ ሲሆን እስካሁን በወረደው አርሶ አደሮች በበልግ እና በመህር እርሻ ልማት በተለያዩ ሰብሎች የሸፈኗቸው ማሳዎች የሚጠበቀው ምርት ሊሰጡ እንደሚችሉ የመስክ ጉብኝት ያደረጉ የአበሽጌ ወረዳ አመራሮች ተናገሩ።

እንደሀገር ያጋጠው የማዳበሪያ እና የምርጥ ዘር አቅርቦት እጥረት ሳያዘናጋቸው አርሶ አደሮቹ ማሳቸውን ከዚህ ቀደም ከሚታወቁበት የጤፍ፣ የበቆሎ፣ የማሽላ፣ የቦለቄ ሰብሎች በተጨማሪ በወረዳው ለመጀመረያ ጊዜ በአኩሪ አተር ሰብል የተሸፈኑ ማሳዎች ይገኙበታል።

በወረዳው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወረዳው አርሶ አደር የማሳ ሽፋን ተሰጥቶት ውጤት እየታየበት የሚገኘው የሩዝ ሰብልም በዘር ከተሸፈኑት ማሳዎች መካከል አንዱ ሆኗል።

የወረዳው አመራሮች በዘር የተሸፈኑ የአርሶ አደሮች ማሳ ላይ የሰብሎች ቁመና ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በማሳዎቹ ላይ የተመለከቷቸው የእርሻ ልማት የምርት ቁመና የሚጠበቀው የምርት ውጤት የሚገኝባቸው መሆኑ ተናግረዋል።

የአበሽጌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መላኩ ብርሃኔ ከመስክ ጉብኝቱ በኋላ እንደተናገሩት እንደ ሀገር ያጋጠመውን የማዳበሪያ እና የምርጥ ዘር አቅርቦት እጥረት ተቋቁመው ውጤታማ የማሳ ላይ ተግባር ለፈፀሙ የወረዳው አርሶአደሮች፣ የግብርና ልማት ባለሞያዎች እና ዘርፉን በቅንጅት ለመሩ በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮች ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

የአበሽጌ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዘመተ አይፎክሩ በበኩላቸው አርሶ አደሩ በማሳው ላይ በሚስተዋለው ውጤታማ የምርት ቁመና ሳይዘናጋ በእርሻ እና በዘር ወቅት ያሳየውን ውጤታማ ስራ ምርቱ ለመሰብሰብ እስኪደርስ እና ወደ ጎተራ እንከሚገባበት ጊዜ ድረስ ትጋቱን አጠናክሮ መቀጠል ይጠበቅበታል ብለዋል።

በማሳው ላይ ሊደርሱ በሚችሉ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ችግሮች ልፋቱ በከንቱ እንዳይቀር አይን እና ሃሳቡን ከማሳው ሳይነቅል ሊጠባበቅ እንደሚገባውም መልእክት አስተላልፈዋል።

በአበሽጌ ወረዳ የጊቤ ይባሬ ቀበሌ አርሶ አደሮች መካከል አርሶ አደር ማሞ ሸዋዬ፣ መቅደስ ጌታሁን እና አርሶ አደር የፀዳው በሰጡት አስተያየት አርሶ አደሩ ጊዜ እና ጉልበቱን በአግባቡ በማሳው ላይ ካዋለ በማሳ ላይ አሁን ከሚታየው ውጤታማ የምርት ቁመና በላይ የሆነ ምርት ማግኘት እንደሚቻል ተናግረዋል።

አርሶ አደሮቹ አክለውም የማሳ እንክብካቤ እና የአረም ቁጥጥር ስራዎችን ሳይዘናጋ መስራት ይገባዋል ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል ሲል መረጃው ያደረሰን የአበሽጌ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *