አርሶ አደሩ ያመለጡትን እድሎች ለማካካስ ትኩረቱ ግብርናው ዘርፍ ላይ ካደረገ በአጭር ጊዜ መለወጥ እንደሚችል በጉራጌ ዞን ምስራቅ መስቃን ወረዳ የደቦና ባቲ ቀበሌ ሞዴል አርሶ አደር ሙህዲን መኩሪያ ተናገረ፡፡

አርሶ አደሩ በአሳ ማስገር ስራ ተሰማርቶ መስራት ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ተመልክቻለሁ ብሏል፡፡

አርሶ አደር የሀገሪቱን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በመደገፍ ላይ የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡

ሰዎች ለምግብነት ከሚጠቀሙት ጀምሮ እስከ ፋብሪካ ግብዓት የሚሆኑ የተለያዩ ምርቶች ስሪታቸዉ ከአርሶ አደሩ ነው፡፡ ይህን ያህል ጠቀሜታ ያለው የግብርና ዘርፍ ታዲያ ጠንካራ አርሶ አደሮችን ይፈልጋል፡፡ ለዚህም በጉራጌ ዞን ምስራቅ መስቃን ወረዳ ዶበና ባቲ ቀበሌ የሚገኘው ሞዴል አርሶ አደር ሙህዲን መኩሪያ ስለ ግብርናው ጠቀሜታ በቁጭት ነው የሚናገረው፡፡
አርሶ አደር ሙህዲን ያሉ ሁለንተናዊ ፀጋዎችን ያለመሰልቸት በመጠቀሙ አሁን ላይ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን ተናግሯል፡፡ ወደ ውጭ ሀገር ተሰድጄም ህይወትን አይቼዋለሁ የሚለው አርሶ አደሩ በራሱም በዘርፉ ላይ የተለያዩ ስነ ዘዴዎችን በመከተል ይሞክራል፣ በባለሙያ የተነገረውን ምክረ ሃሳብም በቅንነት ተቀብሎ ይተገብራል፡፡

ታዲያ በዚህ ወቅት በዞኑ ብሎም በአካባቢው ከተለመዱ የግብርና ዘርፎች ውጭ የአሳ ማስገር ስራ እየሰራ ነው፡፡ የከርሰ ምድር ውሃን በፖምፕ በመሳብ እስከ 12 ሜትር በሚደርስ ማቆሪያ ላይ እያጠራቀመ ነው አርሶአደሩ አሳ እያስገረ የሚገኘው ፡፡
በግብርና ጽ/ቤት አማካይነት 30. የአሳ ጫጩት መጥቶለት በሙከራ ደረጀ አሳን ማርባት የጀመረው አርሶ አደር ሙህዲን አሁን ላይ የአሳዎቹ ብዛት ቁጥር ስፍር እንደሌለው ይናገራል፡፡
ለተዝናኖት ተብሎ የተጀመረው የአሳ እርባታ ከምግብ ፍጆታ አልፎ ለገበያ ሊውል መሆኑን ገልጸው በአሳ ማስገር ስራ ተሰማርቶ በመስራት ውጤታማ መሆን እንደሚቻል አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

አርሶ አደሩ ጥምር ግብርናን ይከተላል፣ የአቮካዶ፣ የፖፖያ፣ የቡና፣ በከብት እርባታ፣ እንዲሁም በበጋና በመደበኛ መስኖና ሌሎችም ዘርፎች ላይ በመሳተፍ ውጤታማ ሆኗል፡፡
በተለይም ይላል ሞዴል አርሶ አደሩ ቀጣይ ወደ ውጭ ኤክስፖርት የሚደረጉ ምርቶችን ለማምረት እቅድ እንዳለው ይናገራል፡፡
በመሆኑም አርሶ አደሩ የአካባቢውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ያመለጡትን እድሎች ለማካካስ ትኩረቱ ግብርናው ላይ ካደረገ በአጭር ጊዜ እራስንም ሀገርንም መለወጥ ይችላል ብለዋል፡፡
ስለዚህ የግብርናውን ፀጋ እንጠቀምበት ይላል አርሶ አደር ሙህዲን፡፡

ወጣት ሙሌ ማሞ በአርሶ አደሩ አማካኝነት የስራ እድል ተፈጥሮለታል፡፡ አርሶ አደሩ በሁሉም ዘርፍ ጠንካራ የስራ እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉም ነው የተናገረው፡፡

በምስራቅ መስቃን ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት የእንስሳትና አሳ ሃብት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነስራላ ነጋሽ አርሶ አደሩ ድጋፍ ቢደረግለት የመቀበልና ተግባራዊ የማድረግ አቅም እንዳለው ገልጸው በተለይም በሙከራ የተጀመረው የአሳ ማስገር ስራና ለሌሎችም እንዲሰፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡

የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሻፊ ሁሴን በበኩላቸው አቶ ሙህዲን መኩሪያ በወረዳው ግንባር ቀደም አርሶ አደሮች መካከል አንዱ መሆኑን ገልጸው ጥምር ግብርና እንደሚከተል ገልጸዋል፡፡

በእንስሳትና አሳ ዘርፍ ላይም ውጤታማ ስራ እየሰራ ይገኛል ያሉት ኃላፊ በዚህ ወቅት አጠቃላይ ካፒታሉ ከፍ ማለቱን ተናግረዋል፡፡

የሚደረገው ድጋፍ ብቁ ባለሙሆኑን በቀጣይ የተጠናከረ ክትትል ተደርጎለት ወደ ኢንቨስትመንት እንዲሸጋገር ይደረጋል ብለዋል ሲል የዘገበው የወልቂጤ ኤፍኤም ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

=ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *