አረፋ (ኧወመያ፣ ኧሙራ) ገበያ በጉንችሬ ከተማ አስተዳደር

ማህበረሰብ ቱባ ባህሉ ፣ የእርስበርስ መስተጋብሩ፣ ስርአቱና ማህበረሰባዊ ስነልቦናው በአደባባይ ለተመልካች ፍንትው አድርጎ ከሚያሳይባቸው ሁነቶች አንዱና ዋናው የግብይት ስርአቱ ነው።

ለጉራጌ ማህበረሰብ ግብይት (ንግድ) ከኢኮኖሚያዊ ትሩፋቱ ባሻገር ጥበብ ነው። ይህንን ጥበብ ከሚገልጥባቸው ትላልቅ የግብይት ሁነቶች መካከል “ሙራ” ወይም የአረፋ በአልን በማስከተል የሚኖር የገበያ አንዱ ነው።

የአረፋ (የወኸመያ) ገበያ መግዛትና መሸጥ ማህበራዊና ስነልቦናዊ እንዲሁ ኢኮኖሚያዊ ግዴታ የሚሆኑበት የገበያ ሁነት ነው።

የገበያ ስርአት (ግብይት ) ጥበብ ስለመሆኑ፣ ድምፅ አውጥቶ የሚጮኸ ውበት ስለመላበሱ በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ የወኸመያ ገበያ ግብይት ምስክር ነው።

በአደባባይ ተሰጥተው የተመልካችን ቀልብ ቅስፍ አድርገው የሚዙ ባህል የወለዳቸው እምቅ የእደ-ጥበባት ውጤቶች፣ የሸማቹን ስነልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቱን አጥብቆ የተረዳ ሻጭ፣ እንዲሁ የሻጩን ሁኔታና ወቅታዊ የገበያ ዋጋ በጥልቀት የተረዳ ሸማች መካከል የሚደረግ ፍጥጫ። በርግጥም የማይደራደር፣ የማይሸጥ፣ የማይገዛ የለም።

ባህልን፣ አብሮነትንና መተጋገዝን ከሁሉ በላይ የጋራ እሴት የሆነው “ወኸመያ” ማዕከል ያደረገ የዋጋ ድርድር በሻጭና በሸማች መካከል ሲደረግ ላስተዋለ፣ ግብይት የገበያ ባለቤት የሆነውን ማህበረሰብ የስነ ልቦና ልህቀት መመዘኛ ስለመሆኑ መረዳት ይቻላል።

በዕለተ አርብ የወኸመያ (አረፋ) ገበያ ቅኝታችን የታዘብነው፣ የተገረምነው፣ የበዛ ቢሆንም አይተንና ሰምተን የማናስቀራቸው የወኸመያ ገበያ ድምቀት የነበሩት ከቤት ማስዋቢያ እስከ ማዕድ ማቅረቢያነት የሚውሉ የባህል ቁሳቁስ፣ የሰንጋ በሬ እና የገበያው ትርምስ በፎቶ እናድርሳችሁ።

በመጨረሻም በዕለቱ ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር ሲከናወንበት የነበረው የእርድ ከብት ገበያ የዋጋ ሁኔታ በከፊል
እ. ከፍተኛ ሰንጋ ሽያጭ 75,000 ….70ሺ
ከፍተኛ 65ሺ..60ሺ
መሀከለኛ ሰንጋ 55ሺ……50
ዝቅተኛ ሰንጋ 45ሺ…..40ሺ
ወይፊን ከፍተኛ…40….35
መካከለኛ….30ሺ……እስከ 25ሺ
ዝቅተኛ 20.ሺ….እና በታች

መሴና ከፍተኛ 45ሺ…40
መካከለኛ 35ሺ…….25ሺ
ዝቅተኛ 20.ሺና ከዚያ በታች ..
መረጃው የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *