አምራቹና ሸማቹን ማህበረሰብ በቀጥታ የሚያገናኘዉ የባዛር ዝግጅት ፋይዳዉ የጎላ መሆኑም የወልቂጤ ከተማ ንግድና ገብያ ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

መስከረም 10/2015 ዓ.ም

አምራቹና ሸማቹን ማህበረሰብ በቀጥታ የሚያገናኘዉ የባዛር ዝግጅት ፋይዳዉ የጎላ መሆኑም የወልቂጤ ከተማ ንግድና ገብያ ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የመስቀል በአል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ምርቾች ለማህበረሰቡ ማቅረባቸዉ በባዛሩ እየተሳተፉ ያሉ አንዳንድ ነጋዴዎች ገለጹ።

የወልቂጤ ከተማ ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አስራት ታደለ እንዳሉት የመስቀል በአል ምክንያት በማድረግ በከተማዉ በየአመቱ የባዛር ፕሮግራም ይዘጋጃል።

በዘንድሮ አመት ባዛሩ የቃቄ ዉርድወት የነጋዴ ሴቶች ማህበር መንግስት ባመቻቸላቸዉ ህንጻ ግንባታ ቦታ አቅም ስላነሳቸዉ ተቋሙ ጉሊት ላይ የሚቸረችሩ እናቶች ለመደገፍና ለማበረታት ከንግድ ዘርፍ ምክር ቤት በጋራ በመሆን ባዛሩ እንዲያዘጋጁ ማድረጋቸዉም አስታዉቀዋል።

በተቋም ደረጃ ኮሚቴ በማቋቋም ለባዛር አገልግሎት የሚዉል ቦታ የማመቻቸትና ወደ ተግባር ተገብቷል ብለዉ በባዛሩ በአካባቢዉ የሌሉ በርካታ ቁሳቁሶች የሚቀርቡበት እንደሆነም ተናግረዋል።

የዞኑ ዋና ከተማ የወልቂጤ ነዋሪዉ ማህበረሰብ ከባዛሩ ጎን ለጎን ለአካባቢዉን ሰላም የሚጠብቅ ሲሆን ከተለያዩ ቦታዎች የሚመጡ የባዛሩ ተሳታፊ እንግዶች በአግባቡ ምርቶቻቸዉን ለማህበረሰቡ እያቀረቡ እንደሆነም ተናግረዋል።

የባህል ዕቃዎችን ከባህልና ቱሪዝም ጋር በመሆን የማስተዋወቅ ስራም እየተሰራ እንደሆነም የተናገሩት አቶ አስራት ከገብያዉ ጋር ተያይዞ በባዛሩ የሚሸጡ እቃዎችን ኮሚቴ ተዋቅሮ ጊዜ ያለፈባቸዉ ምርቶች የመፈተሽና የመከታተል ስራዎችም በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም አስታዉቀዋል።

የቀረቡት እቃዎች ከአምና ደረጃ የተሻሉ እንደሆነም ጠቁመዉ በባዛሩ የሸቀጣሸቀጥ ፣የቤት እቃዎችና ሌሎችም ምርቶች እንደቀረቡም አመላክተዋል።

ባዛር መዘጋጀቱ ፋይዳዉ አምራቹና ሸማቹን ማህበረሰብ በቀጥታ ማገናኘት የሚያስችል እንደሆነና ዋጋዉ ዉጪ ላይ ካለዉ ዋጋ በተወሰነ መልኩ ቅናሽ የተደረገ እንደሆነም ተናግረዋል።

ከአዲስ አበባ ወልቂጤ ድረስ የተለያዩ ለባዛርና ኤግዚቢሽን የሚሆኑ ቁሳቁሶች ይዘዉ የተገኙ ነጋዴዎች አቶ ኤልያስ ፋታ እና አቶ አቢኔዘር መንግስቱ እንዳሉት ማህበረሰቡን የሚጠቀምባቸዉ በርካታ ቁሳቁሶች የመስቀል በአል ምክንያት በማድረግ ለተጠቃሚዎች ማቅረባቸዉም ተናግረዋል።

የኑሮ ዉድነት ለተጠቃሚዎች ከፍተኛ ጫና እየሆነባቸዉ እንደሆነም አስረድተዉ ማህበረሰቡ ባቅሙ የሚችለዉን ዕቃ እየሸመተ እንደሆነም አብራርተዋል።

በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ የመስቀል በአል በከፍተኛ ድምቀት የሚከበር እንደሆነና በዚህም በየአመቱ የድርጅታቸዉ ምርት ይዘዉ በመምጣት ለማህበረሰቡ እንደሚያቀርቡም አስረድተዋል።

ለባዛር አገልግሎት የሚሆነዉ ቦታ ያመቻቹት የወልቂጤ ከተማ የነጋዴ ሴቶች ማህበር ስራ አስፈጻሚና የኮሚቴ አባል ወይዘሮ ጸሃይ ደምስስ እንደተናገሩት የቃቄ ዉርድወት የሴቶች ማህበር በወልቂጤ ከተማ ራስዘስላሴ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ለሚገነባዉ ህንጻ የገንዘብ እጥረት እንደገጠማቸዉም ተናግረዋል።

ይህ ባዛር ለማህበሩ የሚሆን የገቢ እያሰባሰቡ እንደሆነም አብራርተዉ ከወልቂጤ ከተማ ከንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ጋር በመነጋገር ባዛሩና ኤግዚቢሽን በማዘጋጀት ገቢዉ ለቃቄ ዉርደት የህንጻ ግንባታ እንዲሆን በመስማማትና ባዛሩን ለማዘጋጀት ከተማዉ ላይ የነበረዉ ወቅታዊ ችግር ነጋዴዎች በብዛት ለማግኘት ትልቅ ተግዳሮት ገጥሟቸዉ እንደነበረም አብራርተዉ አሁን ላይ በባዛሩ በርካታ ነጋዴዎች ምርቶቻቸዉን ይዘዉ መጥተዉ በባዛሩ እየተሳተፉ
እንደሆነም ጠቁመዋል።

ነጋዴዎች በሚፈልጉት ልክ ማግኘት እንዳልቻሉም የተናገሩት ወይዘሮ ጸሀይ በባዛሩ የወጭ ሀገር ዜጎች ቢሳተፉም የተሻለ ይሆን ነበር ብለዋል።

ማህበረሰቡ በበዛሩ ከተማዉ ላይ የማይገኙ እቃዎችን የሚፈልግ ሲሆን ይህንንም ደግሞ የዉጭ ሀገር ዜጎች ይዘዉት የሚመጡት ዕቃዎች የተለየና የትም ቦታ ሄደዉ ማያገኙት የማችሉት እንደሆነም ጠቁመዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *