ትክክለኛና ወቅታዊ የሶሺዮ አኮኖሚ መረጃ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል በዜጎች መካከል እንዲኖር ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን የጉራጌ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ ገለፀ ።

መምሪያው ለ2015 በጀት ዓመት የሀብት ክፍፍል ግብዓት የሚሆን የሶሺዮ ኢኮኖሚ አመልካች መረጃዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት በወልቂጤ ከተማ የምክክር መድረክ አካሂዷል ።

የጉራጌ ዞን ፕላን ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ከበደ ኃይሌ እንዳሉት የመድረኩ አላማ የ2015 በጀት አመት የበጀት ማከፋፊያ ቀመር መረጃ ለማጥራትና ከዞኑ ሴክተር መስሪያ ቤቶችና መዋቅሮች በመረጃ ልዩነት ዙሪያ መግባባት ለመፍጠር ያለመ ነው።

በተለይም በ2012 በጀት አመትና በ2013 በጀት አመት የነበረውን የመረጃ ልዩነቶችን በዝርዝር በማውጣት ውይይት በማድረግ መግባባት የመፍጠር ስራ መሰራቱን አመላክተው የ2013 በጀት አመት የጠራ መረጃ ለተቋማት የመስጠት ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

አክለውም ከትምህርት ተቋም አንፃር ከተማሪዎችና ከመምህራን ቁጥር፣ ከተማሪ ወንበርና ከተማሪ መምህር ጥምርታ ጋር ተያይዞ ሰፊ ጉድለት መኖሩን ገልፀዋል።

እንደ ኃላፊው ገለፃ የበጀት ክፍፍል ቀመሩ የፌደሬሽን ምክር ቤት የቀመር መረጃ መሰረት በማድረግ መሰራቱን ጠቁመው የሶሺዮ ኢኮኖሚ መረጃ ጥራትና ወቅታዊነት ቀጣይ ለሚደረገው የሀብት ክፍፍል ፍትሃዊ እንዲሆን ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።

መረጃ ሀብት ነው ያሉት ኃላፊው የታችኛው መዋቅር ከመምሪያ ጋር በመናበብ የመረጃ ጥራትና ተገቢነት ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት መስራት እንዳለባቸው ጠቁመው ለዚህም ሶፍትዌር በመጠቀም መረጃ በአግባቡ በማስገባት በየጊዜው ወደ ዞን የሚተላለፉ መረጃዎች ማጥራት አለባቸው ብለዋል ።

ትክክለኛና ተገቢ መረጃ ለማደራጀት የሰው ሀይል፣ ግብአት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው ለዚህም መምሪያው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እንደሚሰራ ተናግረዋል።

መምሪያው ተቋማት የመረጃ አያያዛቸው ጥራትና ትክክለኛ እንዲሆን ለታችኛው መዋቅር ድጋፍና ክትትል ከማድረጉም በተጨማሪ ከወልቂጤ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ስልጠና እንደተሰጠም ገልፀዋል።

የዞኑ የመረጃ ጥራት ያለውና ተገቢ እንዲሆን የመረጃ ስርአቱ ማዘመን እንደሚገባ የገለፁት አቶ ከበደ ለዚህም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ትኩረት በመስጠት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው መምሪያው መረጃዎችን ለማጥራት እየሰራ ያለው ስራ የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመው ተቋማት የመረጃ ጥራትና ትክክለኛነት ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ቀጣይ ለሚደረገው የሀብት ክፍፍል ፍትሃዊ እንዲሆን መስራት አለባቸው ብለዋል።

በመድረኩም የወረዳና የከተማ አስተዳደር የፕላን ፅህፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የሶሺዮ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች፣ የዞን የሚመለከታቸው የመምሪያ ኃላፊዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝቷል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *