ጳጉሜ 4 - የኅብር ቀን
ታላቅ የጎዳና ላይ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ ይካሄዳል!!
ጳጉሜ 4 የኅብር ቀንን አስመልክቶ በጎዳና ላይ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ከ10 ሺህ በላይ ወጣቶች ፣ሴቶች ፣ህጻናት ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ።
በወልቂጤ ከተማ ጷጉሜ 4 ከጠዋቱ 12: 30 ጀምሮ ብዙሃን የሚያሳትፍ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ይካሄዳል ።
እኛ ኢትዮጵያውያን የጋራ ትናንት፡- የጋራ ታሪክ፣ የጋራ ቅርሶች፣ ባሕሎች፣ ኃይማኖቶች እንዲሁም ቁሳዊና ቁሳዊ ያልሆኑ ሐብቶች ባለቤት ነን።
እኛ ኢትዮጵያውያን የትናንት ድላችን፣ የዛሬ ጥንካሬያችንና የነገ ተስፋችን ሚስጥር ኅብር ነው ።
ኅብራዊነት የታሪክ፣ የቋንቋና የባህል ልዩነት አለን ብለው የሚያምኑ ሕዝቦች በህብረት የሚኖሩበት ሁኔታን የሚገልጽ ነው፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያም የተለያየ ማንነት (ማለትም የኃይማኖት፣ የቋንቋ፣ የባሕል) ያላቸው ሕዝቦች፣ ውብና ማራኪ የተፈጥሮ ገጽታ፣ አስደናቂ የብዝሃ ህይወት ክምችት ያላት ሀገር ነች።
ጷጉሜ 4 በዞናችን በወልቂጤ ከተማ የኅብር ቀንን አስመልክቶ እኔም ፣አንተም ፣እነሱም ፣እኛም የምንሳተፍበት ታላቁ የጎዳና ላይ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ነዉ ።
ጷጉሜ 4 ወልቂጤ ከተማ ባሮክ ሆቴል ፊትለፊት ላይ ከጠዋቱ 12:30 እንገናኝ!!
ጳጉሜ 4 – በኅብር ወጥተን በኅብር ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንሰራለን!!