ተያዙ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ ጥራቱን የጠበቀ እቅድና ሪፖርት መዘጋጀት የጎላ ሚና እንዳለው የጉራጌ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ አስታወቀ።

ተያዙ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ ጥራቱን የጠበቀ እቅድና ሪፖርት መዘጋጀት የጎላ ሚና እንዳለው የጉራጌ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያው ለዞን የልማት እቅድ ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት በእቅድ ዝግጅትና ሪፖርት አቀራረብ፣ በካፒታል ፕሮጀክቶች ምልመላና መረጣ ላይ በወልቂጤ ከተማ ስልጠና ሰጥቷል።

እቅድ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፍላጎቶች ለማማላት የጋራ ግቦች እንዲሁም ግቦችን ለማስፈጸም የሚያስችሉ ስልቶች እና ለስራው የሚያስፈልግ ግብዓቶችን መሰረት በማድረግና በማቀናጀት የተፋጠነ ልማት ለማምጣት የሚዘጋጀበት የተግባር መመሪያ ነው፡፡

የጉራጌ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ከበደ ኃይሌ በዚህ ወቅት እንዳሉት የስልጠናው አላማ በእቅድ አስተቃቀድ፣በሪፖርት ዝግጅች፣በካፒታል ፕሮጀክቶች ምልመላና መረጣ ላይ የሚገጥሙ ችግሮች በማስተካከል በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት እንዲያስ አስታውቀዋል።

በተቋማት የሚከናወኑ ስራዎች ውጤታማነት ጥራት ያለው እቅድ ከፍተኛ ሚና አለው ያሉ ሲሆን በቀጣይ ደግሞ አንድ እቅድ አንድ የሪፖርት መርህ በመከተል ለስራዎች ተፈጻሚነት በትኩረት መስራት ይገባል ነው ያሉት።

በየወቅቱ የሚደረጉ ምዘናዎች ተግባር ተኮር ማድረግ እንደሚገባ ያስታወቁት አቶ ከበደ የካፒታል ፕሮጀከቶች ምልመላና መረጣ ጊዜውን ጠብቆ በማዘጋጀት አስፈላጊውን በጀት እንዲመደብላቸው መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ለዚህ ደግሞ አሳማኝ እና ጥራት ያለው መረጃ ማቅረብ እንደሚገባና በየ ተቋማት የተያዙ የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈጻጸማቸው መከታተል እና መገምገም ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል።

የተያዙ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ ጥራቱን የጠበቀ እቅድና ሪፖርት የጎላ ሚና ያለው በመሆኑ በዚህም በትኩረት እንዲሰራ እና በዘርፋ የሚስተዋሉ ችግሮች ማረም እንደሚገባ አቶ ከበደ አስታውቋል።

የመምሪያው የፕላን ዝግጅት ክትትልና ግምገማ የስራ ሂደት አሥተባባሪ አቶ አመሀ ዘርጋው በበኩላቸው በየ ተቋሙ የሚቀርቡ የካፒታል ፕሮጀክቶች ከተቋሙ አላማ እና ግብ የተያያዙና ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናቶችና እቅዶች መሆን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በቀጣይም ድጋፍ ክትትል በማድረግ፣ሙያዊ ስልጠናዎች እንዲሁም ግብረ መልሶችን በማዘጋጀት ቀልጣፋ የመረጃ ልውውጥ በማድረግ ለውጤታማነቱ የበለጠ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በስልጠናው የተሳተፉ አካላት እንዳሉት የህብረተሰቡ የልማት ፍላጎት ለማርካት እንዲሁም የተጀማመሩ ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ ጥራት ያለው እቅድና ሪፖርት እንዲሁም አንድ ሪፖርት አንድ እቅድ ማዘጋጀት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

የህብረተሰቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በካፒታል ፕሮጀከት ስራዎች ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *